Zarem Del Adrgalech, a poem for Birtukan Mideksa by Welelaye

ሬም ድል አርጋለች

ወለላዬ ከስዊድን (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

ንኳን ደስ አላችሁ ብርቱካን ተፈታች፤

ሀገር ምድሩ ይስማ ይህንን ምስራች።

በሠላም አክርሞ በጥሩ ጤንነት፤

ፈጣሪ አምላካችን እንኳን ለዚህ አበቃት።

 

ነገር ግን ብርቱካን ወጣች በመባሉ፤

እንዳለቀ አንቁጠር እንዳበቃ ትግሉ።

ሀገር ሁሉ ታስሯል በጭቆና እግረሙቅ፤

ሁሉም ነፃ ይውጣ ህብረቱን እናጥብቅ።

ብርቱካን ያላትን ጠንካራ ዓላማ፤

የገባችበትን አስፈሪ ጭለማ፤

ስቃይ እንግልቷን የመከራዋን ልክ፤

በልባችን ጽፈን እንዳይረሳን ሰርክ፤

ምሳሌ አድርገናት ያችን ሴት አንበሳ፤

ሽህ ብርቱካን ሆነን አብረን እንነሳ።

ስራና እሷነቷ ይሁነን ማዕከል፤

ይበልጥ እንነሳ በአንድነት ለትግል።

 

የአንድነት እናት ናት የሠላም የፍቅር፤

ኢትዮጵያን ለማዳን የተላከች ከእግዜር።

በሾህ አጥር ታጥራ ተሸፍና እውነት፤

በጥሳ ቆራርጣ ብትሻም ለመውጣት፤

ጊዜው አልረዳትም አልፈቀደም ቀኑ፤

ሀሰት በዓለም ነግሶ በክፍለ ዘመኑ።

ብርቱካንም ቃሏ ከሀሰት ተቆጥሮ፤

ሊያቆያት ቢችልም ድጋሚ አሳስሮ፤

እውነት አስተምራ ሐቅን አሳውቃ፤

ከግፈኞች ወጥመድ ወታለች ፈልቅቃ።

ህዝብም ተቀበላት አንጥፎ ቀጤማ፤

አንዱ ለአንዱ ነግሮ የሰማው ላልሰማ።

ይህንን ሁኔታ ያዩት አቶ መለስ፤

አንድ ቀን መወደድ መቶ ዓመት ከመንገሥ፤

መሻሉን ተረድተው ክፉ ኀዘን ገባቸው፤

ዛሬም ተሸነፉ በገዛ ሥራቸው።

ጊዚያዊ ደስታቸው እሮጠ አመለጠ፤

መሪው አደረጋት ህዝብ እሷን መረጠ።

ይሄንን የሰማ ይበል የምስራች፤

አልተሸነፈችም ዛሬም ድል አድርጋለች።


ወለላዬ

This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ