L. Gen. Bacha Debele

ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ መግለጫውን በሰጡበት ወቅት (ፎቶ፣ ከኢቲቪ ስክሪን ሹት)

(ኢዛ) ሕወሓት በሰሜን ዕዝ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ የፈጸመውን ሰቅጣጭ ተግባር በኢትዮጵያ ውስጥ ይፈጸማል ብሎ ማመን እጅግ ይከብዳል፤ ግን ኾኗል።

በትግራይ ሚሊሻ፣ ልዩ ኃይል አባላት፣ የሠራዊቱ አባላትና ኦነግ ሸኔ የተፈጸመውን ዘግናኝ ተግባር በተመለከተ ዛሬ ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ በሰጡት መግለጫ፤ የመቀሌው ጁንታ ቡድን የፈጸመው ተግባር ምናልባትም በአገሩ ሠራዊት ላይ ጨለማን ተገን በማድረግ የወጋ ብቸኛው የዓለም ታሪክ ሊኾን የሚችል ነው።

ሰሜን የሚገኘውንና ከሕወሓት ጋር እየተዋጋ ያለውን የአገር መከላከያ ሠራዊት ጎብኝተው ወደ አዲስ አበባ የተመለሱት ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ፤ መቀሌ የመሸገው ጁንታው የሕወሓት ቡድን በሰሜን ዕዝ ላይ የፈጸመውን ዘግናኝና አረመኔያዊ ድርጊት አስመልክቶ በዓይናቸው ያዩትንና ያሰባሰቡትን መረጃ ዛሬ ማክሰኞ ኅዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ይፋ አድርገዋል። ለመመልከትና ለማዳመጥ የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ! (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ