ይቅርታሽን ብርቱካን

ጌድዮን በለጡ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. 

የውስጤ ሀፍረት

ውዳሴ ማቅረብ ቢሳነው፤

እንደ ክርስቶስ ተቤዠሽን

ማለት ብቻ ነው የመረጠው።

ያለበደልሽ ይቅር ብለሽ

ውርደታችንን ለበሽው፤

ከሲኦል ጉሮኖ ደጅ ወጥተሽ

እንኩዋን ከእኛው እስር ቤት ተቀላቀልሽ፤

እንኩዋን! እንኩዋን! ለዚህ አበቃሽ

ከጠባቡ ወደ ሰፊው የመዛወር ምህረት ሰጡሽ።

አንች ከስር ስትወጭ

እኛ በፍረት አንገት ደፋን፤

ዝም! ብለን እንደሰጠንሽ

ዝም! እንዳልን መጣሽብን።

ባንች ጽናት ትንሳኤአችንን

ለማብሰር ድፍረቱን አጥተን፤

እንግልትሽ ለኛ ሰቆቃ

መከራሽ ለሁላችን ይሁንብን

ማለት ለተሳነን ለሙላችን፤

ግፍንና ግፈኞችን

ላንዴም እንኩዋን

ደፍሮ መጠየፍ ላቃተን፤

በቃ! ብሎ ቆርጦ ማስቆም ለተሳነን።

ብዙ! ሆነን መዓት!

ህልቆመሳፍርት ነፍስ ይዘን፤

ያንችን ያንድያዋን ብርቱ ቀርቶ

የህጣን ሃሌን ቅዋ ላጣነው፤

መንከላዎስ ላልተቻለን

ለኛ ይብላን እስከወዲያኛው፤

ደግመን ደጋግመን ለሞትነው።

ለስድስት መቶ መኣልት ወሌት

አይውሉ ግፍ ሲዋልብሽ፤

ለመታደግ አቅም ላጣነው።

አንች ምን በወጣሽ እህት ዓለም

እኛ የባርነቱን ውርደት እንሸከም፤

ደግመን ደጋግመን እንፈር

አንገታችን ይሰበር፤

አንደበታችን ይታሰር።

የፍርሃታችንን መዘዝ

ስድባችንን አዝለን እንዙር፤

የጥቃታችንን ምህረት

ተከናንበነው እንዘምር።


ጌድዮን በለጡ

This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ቅዳሜ መስከረም 29 ቀን 2003 ዓ.ም.

Saturday, October 09, 2010

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ