ለፈርኦኑ ይቅርታ (አስራት አብርሃም)
ለፈርኦኑ ይቅርታ
አስራት አብርሃም
“ይቅርታ!”
“ፈርኦን ይቅርታ”
ከሆነማ ጉዳዩ
እርስዎን ማስቀየሟ
‘ይቅር’ - አለማለቷ
“ይቅርታ!”
“ፈርኦን ይቅርታ!”
ብላለች ዛሬ
ሁሉን ነገር ትታ፤
መኖሩ ቢከብዳት ለብቻ ተዘግታ
ከልጅ - ከናት፤ - ካገር ተለይታ።
ሕግም ዳኛም
እርስዎ ስለሆኑ
‘ይቅር’ ይበሉልን
ፈርኦን አይጨክኑ።
ያዕቆብ በበረሃ
በችግር ቢመታ
ይባል ነበር ድሮ
‘ኤፍሬም ነው መከታ’
የዮሴፍ ውለታ
የተረሳ ለታ
“ሃሌ! ሃሌ!” በሉ
አገሩ ተፈታ።
ኤፍሬም ከጥንቱ
ታማኝ ለፈርኦኑ
ግብር የሚያስበላ
ይሁዲ መሆኑ
እንኳንስ እኛ
ይመሰክራሉ፤ ነቢያት ቅዱሳኑ።
አስራት አብርሃም



