ምስጋና (ለብርቱካን ሚደቅሳ)
ምስጋና
(ለብርቱካን ሚደቅሳ)
ጌታቸው አበራ
ላገር ኩራት ቀጣይነት - ለትውልዱ ባላደራ፣
ጊዜ መርጦሽ ለክንውን - ለታሪክ ፈር ዕፁብ ሥራ፣
በለጋነት የናት ጫንቃሽ፣
የአዕላፋታ ዕዳ - ክብር - እንደ ታቦት ተሸክመሸ፣
የስቃይ ቀን ... የጣር ሌሊት ... በፈረቃ አሳልፈሽ፣
ለነፃነት ደማቅ ብርሃን - ቀንዲል ሻማ ሆነሽ በርተሽ፣
ላገር ብለሽ፣ ለእኛ ብለሽ ... እንዳንከስም እንደዋዛ፣
አንድ ራስሽን አሳልፈሽ - ለሰጠሽው ሕይወት ቤዛ ...፤
... ከፍ ይበል ባርኔጣችን ...፣
ጎንበስ እንበል ካንገታችን ...፣
ይታጠፍ ወገባችን ...፣
ክብርት ሆይ! ለፀናሽው ለክብራችን!
ጌታቸው አበራ
መስከረም 2003 ዓ.ም.
(ኦክቶበር 2010)



