አዲሱ የልመና ሚኒስትር

(ጭውውት)

ዳግማዊ ዳዊት

Dollar

ከሚስጥር ኪሴና ከእናቱ መቀነት - በሚያገኘው ሽልንግ

ልጀ ሰይፈ ፋንታ - ልክ እንደ አገሬው ወግ

ጥሩ አርጎ አሳዳገው - ቀንዳሙን ዳሌ በግ።

PM Meles Zenawi's cabinet

 

ሙክቱን ሳናርደው - ወይም ሳንሸጠው

ደርግ የአገሬውን ሰው - በመትረየስ ሲያጭደው

ልጀ ሸፈተና - ኢህአሠ ውስጥ ገብቶ

ድፍን ዓመት ቆዬ - ውጊያው ተበራቶ።

በረሃ ቆይቶ - ጎንደርና ጎጃም - ትግራይም ገስግሶ

ልጀ ሰይፈ ፋንታ - ወልዲያ ተመልሶ

የጀግና አቀባበል - ላደርግ ወሰንኩና

መሸትሸት እንዳለ - ሙከቴን አርጀ

ጠዋት አነጋግ ላይ - ቆዳውን እንዲሸጥ - ሰጠሁት ለልጀ

ከቤታችን ማዶ - ያለውም ነጋዴ - ቆዳውን አየና

ከልጀ ወሰደው - ሰባት ብር ሰጠና።

ከወልዲያ ደሴ - ከደሴ ኮምቦልቻ - ከኮምቦልቻም ሸገር

ከሸገር ጅቡቲ - አርጎ በቀይ ባህር

ተሻግሮ ውጭ አገር - ቆዳው ተሸጠና

በአማሪካ ምድር - የአባ ፋንታ ቆዳ - እጅግ ከበረና

 

የሳልሞን ቸዝ ምስል - የአብርሃም ሊንከን

ላዩ ላይ ተስሎ - አለና ሽቅርቅር

መዳፍ - መዳፍ ያክል - ሆኖ ተቆራርጦ - ሆኖ በብዛት

ተብሎ ተከትቦበት - “ሕጋዊ ገንዘብ ነው - የአሜሪካ ሀብት”

ሚሊዮን መቶ ሽ …

ሃምሳ፤ መቶ ና ሽህ - ላዩ ላይ ተፅፎ

ካዝና ውስጥ ገባ - በጥብቅ ተቆልፎ።

ልጄም ከኢህአሠ - መስማማት አቅቶት

መንገዱን አቀና - ሊገናኝ ከተሃት

እዚያም ሳይሳካ ድርቡሽ አገር ገብቶ - ዓመት እንደቆዬ

አማሪካ ገባ - አለኝ እሱን ያዬ።

ዓመታት ነጎዱ - የእኔም ልጅ ተማረ - በሶላቶ መምር

የምጣኔ ሀብትን - የሚያስችል ምርምር

ከዚያም ባንክ ገብቶ - ሥራ ጀመረና

ለጥቂት ዓመታት - ያሳደገውን በግ - ቆዳ ቆጠረና

የምስር የድርቡሽ - የነጭ ምትሃት - ተሃትን ወንድ አርጎ

መንግሥት ሲገለብጥ - ሰይፈም ሰበብ አርጎ

ከዲ.ሲ. ተሳፍሮ - ኢትዮጵያ ገባና

የመለስ አገልጋይ - መሆን ወሰነና

“ኤክስፐርት” ተብሎ - ትልቁ ካቢኔ

ሲለምን ሰማሁት - ይኽው አየሁ ባይኔ።

የዝያን ዳሌ በጌን - የከበረ ቆዳ

ማስገኘት የሚያስችል - ለአገሪቱ በዕዳ

አልያም ለምፅዋት - ብልሃት ፍለጋ

ሊሠራ የእኔ ልጅ - አገር የሚጎዳ

ዛሬ መለስ ሾመው - ሚኒስትር ነህ አለው

የሸጠውን ቆዳ - ለማኝ አደረገው።


ዳግማዊ ዳዊት

This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

መስከረም 2003 ዓ.ም.

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ