ርግባችንን እንታደጋት (ለብርቱካን ሚደቅሳ) ርግባችንን እንታደጋት!! (ለብርቱካን ሚደቅሳ) የወይራ ቅርንጫፍ አንግባ - መልዕክተ-ሕይወትን ልታበስር፣ የዘንባባ ዝንጣፊ አዝላ - ለፍትህ፣ ለሠላም ... ለፍቅር፣ የሁሉን ልብ ስታማልል - የሠላም የእኩልነት ዓርማችን፣ አየሩን ቀዝፋ ስትበር - ንፅህት፣ ፀዐዳ ርግባችን፤ በጨለመው ”መርከብ” ታክቶ - ብርሃን ሕይወት የናፈቀው፣ ላሳየችው ብሩህ ተስፋ - ሀገር ምድሩ ደስ ሲለው፤ እባብ ብቻ ቂሙን ቋጥሮ - ሊያሰናክል ከጉዞዋ፣ በጨለማ ጠፍንጓት - ስለበዛ መከራዋ፣ ያገር አድባር ሳይቆረጥ - ሳይመጣብን ከንቱ መዐት፣ አቤት! አቤት! እንላለን - ርግባችንን እናድናት!! ጌታቸው አበራ ሚያዝያ 2002 ዓ.ም. (አፕሪል 2010 እ.ኤ.አ.) ቀዳሚው ቀጣዩ Tweet