ጠግበሻል ይሉሻል

ፍቅሩ

ጠግበሻል ይሉሻል

ግና ተርበሻል

ጠውልገሽ እያለሽ

ይወራል መውዛትሽ

ተነሳሽ ይሉሻል

አንች ግን ወድቀሻል

ሕመምሽን ሳያውቁት

ፈውስሽን አወጁት

በራብ በቸነፈር ታብተሽ እያለ

ዕድገትሽ ተባለ እያደር አየለ

መች ይሆን ኢትዮጵያ ከሕመምሽ ሽረሽ

ከአንገትሽ ተቃንተሽ ኮርተሽ የምናይሽ?

መቸስ ይሆን ቀኑ

ማብቂያው ሰቀቀኑ?


ፍቅሩ

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ