የኀዘን እንጉርጉሮ

አስፋወሰን ዓለምሰገድ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

 

ከሰባ ዓመት በፊት በየካቲት ወራት

ከጣሊያን የመጣው ቀዳማዊው ፋሽስት

አሥራ ሁለት ሺ ሰው የጨፈጨፈባት

አዲስ ከተማችን ዛሬስ መቼ አደላት

መለስ የተሰኘው ዘመናዊው ፋሽስት

በአሥራ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሰባት

ሳይለይ ሽማግሌ ህፃን እና ወጣት

በጠራራው ፀሐይ በጥይት ሰዋባት።

 

ለዛች ምስኪን እናት ምን ብዬ ልንገራት?

ልጅሽ ሞተ እንዳልል አያውቅም ታሞባት

እንደ ወጣ ሲቀር ወያኔ ቀስፎባት

ኧረ እኔስ ጨነቀኝ እንዴት ብዬ ላርዳት?

 

ወንድምህ ተመትቶ ሊሞት ነው ሲሉህ

እየበረርክ ስትሄድ ስጋ ሆኖብህ

ወያኔ ጨካኙ ትንሽ የማይራራ

አንተንም ቀሰፈህ ከወንድምህ ጋራ።


 

ከግንቦት 1997 ምርጫ በኋላ በግፍ ለተገደሉ ወገኖቻችን መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የተጻፈ

”ህዝባችንን ልቀቅ” ከተሰኘው የግጥም መደብል የተወሰደ

መጽሐፉ የታተመው Sepetember 2005

ደራሲ - አስፋወሰን ዓለምሰገድ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ