የፍቅር ንጉሥ (አስፋወሰን ዓለምሰገድ)
የፍቅር ንጉሥ
(የኀዘን እንጉርጉሮ)
በአስፋወሰን ዓለምሰገድ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
ልክ እንደ ነገሥታት፣ ሠራዊት ባይኖርህ
በአንደበትህ ለዛ፣ በሚስበው ድምፅህ
ህዝብህን በፍቅር፣ በውዴታ ገዝተህ
አወይ የአንተ ነገር፣ በድንገት ተለየህ።
የህዝብህን ደስታ፣ ኀዘኑንም ጭምር
በዘመንህ ሁሉ፣ ተካፍለህ ስትኖር
ዛሬ በቃኝ ብለህ፣ ጥላሁን ለምን ነው?
የተጓዝክ ጥለኸን፣ ድንገት ሳናስበው።
ጥላሁን ገሠሠ፣ እያለህ በሕይወት
ለውዷ ሀገርህ፣ በጣም ለምትወዳት
አቅም ባይፈቅድልህ፣ በአልማዝ ልታስጌጣት
ግዳጅ ሲሆንብህ፣ ቆርጠህ ልትለያት
ከእሩቅ ሀገር መጣህ፣ ደህና ሁኝ ልትላት።
ጥላሁን ደህና ሁን! ኑርም ያለጸጸት
ለኢትዮጵያ ደክመሃል፣ ስትኖር በሕይወት
የህዝብህም ፍቅር፣ ስንቅ ይሁንልህ
ቸሩ እግዚአብሔርም፣ መንግሥቱን ያውርስህ!!!
ለክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ የተደረሰ
በአስፋወሰን ዓለምሰገድ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
04 / 23 / 2009



