አሥራት አትረሳም

አስፋወሰን ዓለምሰገድ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

ፕሮፌሠር አስራት ሞተ ብለው

አረዱኝ ከእንቅልፌ ቀስቅሰው።

መቼ አሥራት እንደሰው ይሞታል

ከኢትዮጵያ ጋር ለዘለዓለም ይኖራል።

አሥራት ወገኑን ሲያክም በወጣትነቱ

እናቱ ታመመች ሲደክም ልበቱ።

 

እንዲህ ነው ሰው መውደድ፣

እንዲህ ነው ፍቅር፤

ሕይወትን ሰውቶ ለማዳን መጣር።

 

አሥራት ሲባል ይመስለኝ ነበር

የቤተክርስቲያን መባ እና ግብር፤

ለካስ አሥራት ቅዱስ መስዋዕትም ይሆናል

ሥርዓቱ በኢትዮጵያኖች ዘንድ ተጀምሮአል።

 

ሁሉም ይሞታል አፈርም ይሆናል

የከፈለ አሥራቱን ከሙታን ይነሳል።

 

የግብር አሥራትን ካች አምና ከፍለን

ለምን እንላለን በዕዳ ተያን።

 

ትንሹም ትልቁም ነፍሱን ያከብራታል

አሥራት ግን ንቆታል ይገርማል ይደንቃል

የቴዎድሮስን ፈለግ ፈሩን ተከትሏል።

 

በስጋ እናታችን ጡት ባጠባችን

አምጸን ወይነን አጉል ታብየን

አሥራቷንም ነጥቀን ተካፍለን በልተን

እግዚአብሔር ተቆጥቶ ይኸው በተነን።

 

ምንም ቢጠቋቁር ቢገረጣ ገጹ

አሥራት እንዲህ አለ በሰለለ ድምፁ፤

”ዋስ ጠበቃም የለሽ ብቻሽን ቀርተሻል

ልጆችሽ ከሰውሽ እጅግ ታውከሻል

እምዬ ኢትዮጵያ እጆንሽን ዘርጊ

ከቸሩ እግዚአብሔር መፍትሔ ፈልጊ።”

 

አሥራት ወልደየስ የሀገሩን ብሶት

ለሰዎች ተናግሮ አንሰማህ ቢሉት

ተጓዘ ነጎደ ወደ እግዜር ችሎት

ቅን ፈራጅ ለሆነው አቤት ለማለት።


"ህዝባችንን ልቀቅ” ከተሰኘው የግጥም መደብል የተወሰደ

ደራሲ አስፋወሰን ዓለምሰገድ

የታተመው September 2005 (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ