እሽሩሩ

አስፋወሰን ዓለምሰገድ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

እሽሩሩ ...

እሽሩሩ ...

እሽርሩ ማሙዬ ...

ልንከባከብህ ’እሽሩሩ ...’ ብዬ

አባት ሆኛለሁ በተራዬ።

 

የአባቴን ፍቅር ባንተ አየሁት

የፍቅሩን መጠን ተረዳሁት

በል እንግዲህ እደግልኝ

የአባቴ ምትክ ስለሆንከኝ።

ስታለቅስብኝ ምርር ብለህ

የሚናገር አፍ ስለሌለህ

ይጨንቀኛል ይጠበኛል

የማደርገው ይጠፋኛል።

 

ስትስቅልኝ እኔን አይተህ

ባባትነቴ ተደስተህ

ልቤ በኀሴት ይፈነድቃል

ለካ ከልጅ ደስታ ይገኛል።

ልመርቅህ ማሙሽዬ

ለወግ ለማዕረግ ያብቃህ ብዬ

እኔ አባቴን እንደተካሁ

አንተም እኔን እንድትተካ እመኛለሁ።

 

ልጅ ፍቅሬ እባክህን

እናፍቃለሁ ፈገግታህን

ጉንፋን እንኳን እንዳይዝህ

እመኛለሁ እኔ አባትህ።

 

አባቴ ይወደኝ ነበር በልጅነቴ

ሳይቀየመኝ በጥፋቴ

እኔም በተራዬ እንደ አባቴ

በልጄ ፍቅር ጋየ አንጀቴ።

ልጅ ለካ የደስታ ምንጭ ነው

አወይ! ቀርቶብኝ እስከ ዛሬ ሳላውቀው።


 

”ፀሐይ ትወጣለች” ከተሰኘው የግጥም መደብል የተወሰደ

መጽሐፉ የታተመው July 2008

አስፋወሰን ዓለምሰገድ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ