ዓባይ

ብርዞ - ከፍራንክፈርት This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

 

ዓባይ የምድረ ንስር ሲሳይ

የጥቁር አፈር ሽታ የሰሜን ተራራ ክፋይ

የከርሰ ጦቢያ ውልድ የምህተዓመት ፍሰት

የሥልጣኔ ዓሃዱ የሰብህና ጅምር እውነት

 

የጠመዝማዛ ጉዞ ዜማ የውሃ ሳቅ ትርዒት

የእምይ ጦቢያ እምብርት ማራኪ ቀለም ውበት

የእንዶድ ፏፏቴ ዝላይ የአምቁ ጢስ ምትሓት

የሕዋ ምድር ተምሳል የማይጠገብ ትዕይንት

 

ባለከበረው ድንጋይ ደንደሳም ባለደለል

ብድግ ወረድ ዘርገፍ ፈንጠር ጎምለል ከብለል

ጦብያ እናትህን እያት አንገትህን አርገው ዞር

ሸክምህን አራግፈህ አስተውላት ባንተ ትታደግ ትጦር

 

የባጎረስኩኝ እጄን ተረት ያድካሚው ጉዞ ምላሽ

የትውልድ ስጋት ፈተና አትሆንም ፍፁም ጭራሽ

አረንጓዴውን ራዕይ የነፍስ አድኑን ተስፋ

በተቀደሰ ምድርዋ ላይ ታደርገዋለህ ይፋ


 

ብርዞ ከፍራንክፈርት This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ