“እኔን አፈር - ይብላኝ” (አባ ቤክሲሳ)
“እኔን አፈር - ይብላኝ”
አባ ቤክሲሳ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
ብርቱ!
ወላፈን ሲጋረፍ ሙቀት ሲበረታ
ተመልካች ሲያላዝን ለፍርሃት ሲረታ።
ከተንቦለቦለው ከግለቱ መሃል
አሳልፋ ሰጥታ ራሷን ለነበልባል።
ከሞት ያዳነችኝ
ነገን ያኖረችኝ
እሳት የበላትን
የእውነቷን ‘እቴቴ’ን -
እህቴን መሰልሽኝ።
በርቺ ብርቱ-ከኔ!
አትታመሚብኝ አትድከሚ እንደሰዉ
ኑሪ ለዘላለም ሞት-ሽን ልውረሰው።
ዕብሪት በለስ ቀንቶት ሲተብት ንጉሡ
ከልጅሽ በልጦብሽ ቃልሽ ከነጦሱ፣
ዱራ ሲመፃደቅ እኩይ ባንቺ ሲናኝ
ቆሞ ታዛቢውን “እኔን አፈር-ይብላኝ”።
አባ ቤክሲሳ
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.



