የሃያ ዓመት ውሸት (ባዩህ ዛሬ)
የሃያ ዓመት ውሸት
ባዩህ ዛሬ
መለስ አባት የለው፤
መለስ በእርግማን ቢሆን በፀሎት
ቀድሞውን ባልገባ ከቤተመንግሥት።
የብረት ምሰሶ አይነቅዝም ያሉት
ማን ይነካው ነበር ደርግን በጉልበት።
በሰው ፍቅር ቢሆን በእምነት በአምልኮት
ራስታ ጀማይካ ኃይሌን ባቆዩት።
እንኳንም ተጠልቶ ህዝብን አስመርሮ
እምዬ ምኒልክ ዮሐንስም ኖሮ
አልቀረም ማለፉ በቀነ ቀጠሮ።
ሁሉም ገደብ አለው የጫወታ መግቻ
መለስ አባት የለው ነጋሪ ለብቻ
ተውጦ ሊተፋ በህዝባዊ ዘመቻ
አፍጦ ይጠብቃል ተጎልቶ እንደ ጉልቻ።



