ዝምታህ ጮኸብኝ

ዳግማዊ ዳዊት

አንተ ፀጥ ያልከው ሰው - አንት የተሎጎምከው

አጥርህ ዙሪያ ታጥሮ - በርክን የዘጋኸው

ሰው መሃል ሆነህ - ከሰው ልጅ የራከው

 

 
ለምስጋናም አሜን

ለእርግማንም አሜን

አሜን በፀጥታህ - አሜን አሜን ያልከው

ዝምታህ ጮኸብኝ - ጆሮየውን በጠሰው

እባክህ ተናገር - ዝምታህም ያብቃ

ዝምታ ትብብር - ከበዳይ አለቃ

መሆኑን እወቀው - የዝምታ ደሞዝ

ዝምታ ጠላት ነው - ይኸን እወቅ ጎበዝ።

 

ነጎድጓድ ባልሰማም - የመብረቅ ብልጭታ

የአውሎ ነፋስ ጩኸት - የዝናብ እሩምታ

መርዶን- ተከትሎ - ደረት ባይመታ

“ወየው ወይኔ!” ባይኖር እንባም መንታ መንታ

ዝምታ ረብሻ ነው - ከጩኸት የበዛ

ህሊናን በጭንቀት - ሰው በአሳር የገዛ።

 

አወይ ገለልተኛ - አወይ ትርምሱ - አወይ ግሳንግሱ

የዝምታ ጓዙ - በየትኛው ድልድይ - ይሻገራል እሱ

ከእኛ እሚባል እኛ - አሻግሮ የሚያይ ጠፍቶ

ልዩነት ይታያል - ከአንድነቱ ጎልቶ

አወይ ገለልተኛ - ምነዋ አንናገር - አንደበት ተዘጋ

ለአገራችን ጉዳይ - ማንስ ለእኛ ያውጋ

ምነው ዝም የምንል - ህዝብ እየተወጋ?

 

አሜን በፀጥታህ - አሜን አሜን ያልከው

ዝምታህ ጮኸብኝ - ጆሮየውን በጠሰው

እባክህ ተናገር - ዝምታህም ያብቃ

ዝምታ ትብብር - ከበዳይ አለቃ

መሆኑን እወቀው - የዝምታ ደሞዝ

ዝምታ ጠላት ነው - ይኸን እወቅ ጎበዝ።


ዳግማዊ ዳዊት

This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ግንቦት 2002 ዓ.ም.

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ