የጣልያን ውድቀት (ጌቱ)

የጎንደር ጦርነት የአርበኞች ድል የፋሽስት ጣልያን የመጨረሻ ውድቀት

ኃብተሥላሴ ስለሺ (ጌቱ) ከፓሪስ - ፈረንሣይ

ወራሪው የፋሽስት ጣልያን ጦር በጀግኖች አርበኞች ተጋድሎና በእንግሊዝ ረዳትነት ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፲፱፻፴፫ ዓ.ም. ድል ሆኖ አዲስ አበባን ከለቀቀ በኋላ፤ የተቀረው የጠላት ጦር የምስራቅ አፍሪካ የጣልያን ጦር የበላይ አዛዥ በሆነው በዱክ ዲዎስታ አመራር ስር ደሴ ላይ መሽጎ ሲጠባበቅ፤ የቀረው ጦር እንዲሁ የምስራቅ አፍሪካ ምክትል ጦር አዛዥ በሆነው በጄኔራል ናዚ አመራር ጎንደር ላይ መሽጎ የሙሶሎኒን እርዳታ ይጠባበቅ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዓድዋ ድልና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ

የዓድዋ ድልና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪካዊ ድርሻና ውለታ

ፍቅር ለይኩን ከደቡብ አፍሪካ

የዓድዋ ድልን በማስመልከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ን በስንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ በማኅበረ ቅዱሳን የምርምርና የጥናት ማእከል ድሉን አስመልክቶ ቤተ ክርስቲያኒቱ የነበራትን ሚና ለማዘከር በአዲስ አበባ በብሔራዊ ሙዚየም የተደረገውን ውይይት ዜና በደጀ ሰላም ማንበቤ በውስጤ አንድ ስሜት አጫረብኝ፤ እናም ስለ ድሉና ቤተ ክርስቲያናችን ስለነበራት ታላቅ ድርሻና ወለታ ጭምር ጥቂት ለመጨመር አስብኩና ብዕሬን አነሳሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዝክረ አድዋ በኪነጥበብ መወድስ (ዳንኤል አበራ)

ዳንኤል አበራ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

ኢትዮጵያ ከዘመነ መሣፍንት ተላቅቃ አንፃራዊም ቢሆን ወደ ተረጋጋ ማዕከላዊ አስተዳደር የተሸጋገረችበት ዘመን። አባ ዳኘውም እምዬም እየተባሉ ሲጠሩ የነበሩት አፄ ምኒልክ ሥልጣን ያደራጁበት እና ኢትዮጵያን ያሰሱ አውሮፓውያንን ባላሰለሰ የመሣሪያ ስጦታም ግዢም ጥያቄ የወተወቱበት ዘመን፤ ኋላም ተክለፃዲቅ መኩሪያ እንደጻፉልን “ባመጣው ወጨፎ ባመጣው እርሳስ ተፈጠመ ጣሊያን አበሻ እንዳይደርስ” ከተባለበት የጣሊያን መንግሥት ጭምር የመሣሪያ ስጦታ ተረክበው ምኒልክ ጦራቸውን ያደራጁበት ዘመን፤ አውሮፓውያን አህጉራትን እንደቅርጫ ሥጋ የተከፋፈሉበት ዘመን። አፍሪካም፣ ኢትዮጵያም የዚህ ዕጣ ፈንታ ተቋዳሽ እንዲሆኑ በዝግ ተወስኖ ለአፄ ምኒልክና መንግሥታቸው መልዕክት የተነገረበት ዘመን፤ አፄ ምኒልክም መልዕክቱን ሰምተው እግዜር ይስጥልኝ ውሳኔያችሁን አልቀበልም ያሉበት፣ የጦርነትም ስጋት ያንዣበበት ዘመን ነበር ዘመኑ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በዓለ መስቀል

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሠላም አደረስዎ! … “መስከረም ባበባው ሠርግ በጭብጨባው ይታወቃል” ይላሉ አበው። አንድም መስከረም ርዕሰ ዓውደ ዓመት፣ የዘመን መለወጫ በመሆኑ ወርኃ አደይ ወወርኃ ጽጌ ተብሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዛሬ 92 ዓመት ይኼን ጊዜ

“... በታሪክ መድረክ ሚናቸውን ተጫውተው ያለፉ ሰዎች እንደ ተውኔት ገፀ ባህርያት ናቸው። ስለሆነም የዕለት ተዕለት ሰብዓዊ ግኑኝነቶችም ሆኑ በመሪና ዜጋ መካከል ያለው ግንኙነት ኅሊናችንን ሳይጫነው ልንፈርድባቸውም ሆነ ልንፈርድላቸው ይገባል ...” ያሉት እውቁ የታሪክ ሊቅ ፕሮፌሠር ባህሩ ዘውዴ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...