ዳንኤል አበራ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

ኢትዮጵያ ከዘመነ መሣፍንት ተላቅቃ አንፃራዊም ቢሆን ወደ ተረጋጋ ማዕከላዊ አስተዳደር የተሸጋገረችበት ዘመን። አባ ዳኘውም እምዬም እየተባሉ ሲጠሩ የነበሩት አፄ ምኒልክ ሥልጣን ያደራጁበት እና ኢትዮጵያን ያሰሱ አውሮፓውያንን ባላሰለሰ የመሣሪያ ስጦታም ግዢም ጥያቄ የወተወቱበት ዘመን፤ ኋላም ተክለፃዲቅ መኩሪያ እንደጻፉልን “ባመጣው ወጨፎ ባመጣው እርሳስ ተፈጠመ ጣሊያን አበሻ እንዳይደርስ” ከተባለበት የጣሊያን መንግሥት ጭምር የመሣሪያ ስጦታ ተረክበው ምኒልክ ጦራቸውን ያደራጁበት ዘመን፤ አውሮፓውያን አህጉራትን እንደቅርጫ ሥጋ የተከፋፈሉበት ዘመን። አፍሪካም፣ ኢትዮጵያም የዚህ ዕጣ ፈንታ ተቋዳሽ እንዲሆኑ በዝግ ተወስኖ ለአፄ ምኒልክና መንግሥታቸው መልዕክት የተነገረበት ዘመን፤ አፄ ምኒልክም መልዕክቱን ሰምተው እግዜር ይስጥልኝ ውሳኔያችሁን አልቀበልም ያሉበት፣ የጦርነትም ስጋት ያንዣበበት ዘመን ነበር ዘመኑ።

 

የኢትዮጵያ ህዝብ ከኅዳር በሽታ ያገገመበት፤ እውነት መሆኑን ያላረጋገጥኩት ግን ጣሊያኖች ባመጧቸው የታመሙ ከብቶች የኢትዮጵያ ከብቶች ያለቁበት፣ ረሃብ ነግሦ ህዝቡንም ደቋቁሶ መንሠራራት እየታየ ያለበት ወቅት ነበር ዘመኑ። (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ