ዛሬ ሦስት ሰዎች በኮሮና መያዛቸው ይፋ ኾነ

Total Coronavirus Cases in Ethiopia

በአገሪቱ በበሽታው የተያዙት ቁጥር 194 ደረሰ

ኢዛ (ዓርብ ሚያዝያ ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 8, 2020)፦ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ከተደረገላቸው 1,861 ሰዎች ውስጥ ሦስት በቫይረሱ የተጠቁ አዳዲስ ሰዎች መገኘታቸውን የጤና ሚኒስቴር ዛሬ ይፋ አደረገ። በአገሪቱ በበሽታው የተያዙት ቁጥር 194 ደርሷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ በረከት የስድስት ዓመት፣ አቶ ታደሰ ደግሞ የስምንት ዓመት እስራት ተፈረደባቸው

Bereket Simon and Tadese Kassa

የፍርድ ቤቱ በገንዘብም እንዲቀጡ ወስኗል

ኢዛ (ዓርብ ሚያዝያ ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 8, 2020)፦ በእነአቶ በረከት ስምኦን የክስ መዝገብ ሲመለከት የነበረው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፤ ዛሬ ዓርብ ሚያዝያ 30 ቀን ከእነአቶ በረከት ስምኦን ላይ የስድስት ዓመት እስር ሲፈርድ፤ በአቶ ታደሰ ካሣ ላይ ደግሞ የስምንት ዓመት የእስር ፍርድ ወሰነባቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አብን የሽግግር መንግሥት መፍትሔ አለመኾኑን ገለጸ

አብን

ምርጫ እስኪደረግ አሁን ያለው መንግሥት መቀጠሉ አንጻራዊ መፍትሔ ነው ብሏል

ኢዛ (ሐሙስ ሚያዝያ ፳፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 7, 2020)፦ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ኢትዮጵያ አሁን ለገባችበት ፖለቲካዊ ቀውስ አዲስ የሽግግር መንግሥት መፍትሔ ይኾናል የሚል እምነት እንደሌለው አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በትግራይ ክልል አራት የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ተገኙ

This illustration, created at the Centers for Disease Control and Prevention (CDC)

ይህም በአንድ ቀን ቫይረሱ የተገኘባቸውን 29 አድርሶታል

ኢዛ (ሐሙስ ሚያዝያ ፳፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 7, 2020)፦ በዛሬው ዕለት የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 25 ግለሰቦች በተጨማሪ፤ በትግራይ ክልልም አራት በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች መገኘታቸውን የትግራይ ጤና ቢሮ በማስታወቁ፤ ባለፉት 24 ሰዓታት በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 29 መድረሱ ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ብዙዎችን ያስደነገጠው ሪፖርት

3ዲ (3D) ኮሮና ቫይረስ በምስል (© istock.com/Dr_Microbe)

በ24 ሰዓት ውስጥ 25 የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ተገኙ

ኢዛ (ሐሙስ ሚያዝያ ፳፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 7, 2020)፦ የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ መከሰቱ ከተገለጸበት መጋቢት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. ወዲህ በብዙዎች ዘንድ ድንጋጤ የፈጠረው ዛሬ የተደረገው ሪፖርት ነው ማለት ይቻላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢዜማ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ያለውን አቋም የሚገልጽ መግለጫ አወጣ

ኢዜማ

ፓርቲው በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 104 እና 105/2 መሠረት የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ማድረግ የሚል አማራጭ ሐሳብ ላይ ተስማምቷል

ኢዛ (ረቡዕ ሚያዝያ ፳፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 6, 2020)፦ ኢዜማ (የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ) ከወቅታዊ የአገሪቱ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የፓርቲውን አቋምና መኾን ይገባዋል ብሎ የሚያምንባቸውን እርምጃዎች የሚያመለክት መግለጫ ዛሬ አውጥቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አስደንጋጩ የጤና ሚኒስቴር ሪፖርት

Total coronavirus cases in Ethiopia, 2020-05-06

በ24 ሰዓት በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ 17 ኢትዮጵያውያን ተገኙ

ኢዛ (ረቡዕ ሚያዝያ ፳፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 6, 2020)፦ የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ መከሰቱ ከተሰማበት ዕለት ጀምሮ በ24 ሰዓት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የቫይረሱ ተጠቂዎች መገኘታቸው ይፋ ኾነ። ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ቀን በቫይረሱ የተጠቁ 17 ሰዎች ተገኙ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከፑንትላንድ የመጡ ሦስት ኢትዮጵያውያን የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

Total coronavirus cases in Ethiopia, 2020-05-04

አምስት አዳዲስ ተጠቂዎች ተገኝተዋል፤ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 140 ደረሰ

ኢዛ (ሰኞ ሚያዝያ ፳፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 4, 2020)፦ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ1,758 ለሚኾኑ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው፤ አምስት የቫይረሱ ተጠቂዎች በመገኘታቸው በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 140 ደረሰ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እነበረከት ስምኦን ጥፋተኛ ተባሉ

አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሣ

የቅጣት አስተያየት ይዘው እንዲቀርቡ ከነገ ወዲያ ተቀጥረዋል

ኢዛ (ሰኞ ሚያዝያ ፳፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 4, 2020)፦ የጥረት ኮርፖሬትን ጥቅም በሚጎዳ መንገድ ተንቀሳቅሰዋል በሚልና ከዚሁ ጋር በተያያዙ አራት ክሶች ቀርቦባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ የቆዩት አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሣ በተከሰሱበት ክስ ጥፋተኛ ተባሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፖሊስ ራስዋን ንግሥተ ነገሥት በምትለው ግለሰብ ላይ ተጨማሪ መረጃ ሰጠ

እኅተ ማርያም

“ወ/ሮ ትዕግሥት ፍትሕአወቅ እንግሊዛዊት ነች፤ የኢትዮጵያ ዜግነት የላትም” ፖሊስ

ኢዛ (ዓርብ ሚያዝያ ፳፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 1, 2020)፦ ራስዋን ንግሥተ ነገሥት ዘ ኢትዮጵያ በሚል በመጥራት ስትንቀሳቀስ የነበረችውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ያዋለው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራዬን ቀጥያለሁ አለ። ስሟ ወ/ሮ ትዕግሥት ፍትሕአወቅ እንደኾነ፣ እንግሊዛዊት እንደኾነችና የኢትዮጵያ ዜግነት እንደሌላት ፖሊስ ገልጿል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ