ኢትዮጵያና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ግስጋሴ

Total coronavirus cases in Ethiopia, May 28, 2020

በአንድ ቀን 100 በቫይረሱ የተጠቁ ተገኙ፤ 94ቱ ከአዲስ አበባ የተገኙ ናቸው

ኢዛ (ሐሙስ ግንቦት ፳ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 28, 2020)፦ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሥርጭት በኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ አስጊ ወደሚባል ደረጃ እየተሸጋገረ ስለመኾኑ አመላካች ሪፖርቶች እየወጡ ሲሆን፣ በዛሬው የጤና ሚኒስቴር ዕለታዊ መረጃ በአንድ ቀን 100 የሚኾኑ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች መገኘታቸውን አሳውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ጤና ኮሌጅ በማዕረግ ተመራቂዋ ወጣት ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ

Addis Ababa Police Commission

የተለያየ የሰውነት ክፍሏን በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ተወግታ ነው የተገደለችው

ኢዛ (ረቡዕ ግንቦት ፲፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 27, 2020)፦ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የጤና ኮሌጅ የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪ ወጣት በቤተ ሙከራ ውስጥ በስለት ተወግታ ሕይወቷ እንዳለፈ ገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ግዴታ መኾኑን የሚደነግግ መመሪያ ጸደቀ

Face mask

መመሪያው ከዛሬ ጀምሮ በሥራ ላይ ውሏል

ኢዛ (ረቡዕ ግንቦት ፲፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 27, 2020)፦ በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ከቤት ውጭ በማንኛውም ቦታዎች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ግዴታ መኾኑን የሚደነግግ መመሪያ ጸደቀ። መመሪያው ከዛሬ ጀምሮ በሥራ ላይ ውሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኮሮና ወረርሽኝ በኢትዮጵያ አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል

3ዲ (3D) ኮሮና ቫይረስ በምስል (© istock.com/Dr_Microbe)

በአንድ ቀን 88 አዳዲስ ተጠቂዎች ተገኙ
55ቱ የውጭ ጉዞ ታሪክም ኾነ ንክኪ የሌላቸው ናቸው

ኢዛ (እሁድ ግንቦት ፲፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 24, 2020)፦ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ከመቼውም ጊዜ በላይ አስጊ መኾኑን የሚያመለክትና በአንድ ቀን ብቻ 88 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የዛሬው የጤና ሚኒስቴር ሪፖርት ይፋ አደረገ። በአገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 582 ደርሷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአዲስ አበባ ቫይረሱ ጎልቶ በሚታይባቸው አካባቢዎች ገደብ ሊጣል ነው

Total coronavirus cases in Ethiopia, May 23, 2020

ዛሬ በኢትዮጵያ 61 ተጠቂዎች ሪፖርት የተደረገበት ቀን ኾኗል
ከ61ዱ 45ቱ ከአዲስ አበባ ናቸው

ኢዛ (ቅዳሜ ግንቦት ፲፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 23, 2020)፦ በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ጎልቶ የታየባቸው አካባቢዎች የእንቅስቃሴ ገደብ ሊጣል እንደሚችል ተገልጿል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከባንክ በጥሬ የሚወጣ ገንዘብ ገደብ ተጣለበት

Dr. Yinager Dessie

ግለሰብ በቀን 200 ሺህ፣ ኩባንያዎች በቀን 300 ሺህ ብቻ ማውጣት ይችላሉ

ኢዛ (ማክሰኞ ግንቦት ፲፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 19, 2020)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገንዘብ አስቀማጭ ግለሰቦችና ኩባንያዎች በየዕለቱ ከባንኮች የሚያወጡትን ጥሬ ገንዘብ የሚገድብ አዲስ መመሪያ ከዛሬ ግንቦት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ሥራ ላይ አዋለ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በትግራይ ከአስቸኳይ አዋጁ ጋር በተያያዘ በፖሊስ ሁለተኛ ሰው ተገደለ

መቀሌ

የትግራይ መገናኛ ብዙኀን እስካሁን ስለጉዳዩ አልዘገቡም

ኢዛ (ሰኞ ግንቦት ፲ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 18, 2020)፦ በትግራይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ድንጋጌዎችን ለማስከበር በሚል በተፈጠረ ግጭት በመቀሌ አንድ ሰው ሲሞት፤ ሁለት መቁሰላቸው ተረጋገጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአንድ ቀን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ 35 ሰዎች ተገኙ

Total coronavirus cases in Ethiopia, 2020-05-08

29ኙ በአዲስ አበባ የተገኙ ናቸው

ኢዛ (ሰኞ ግንቦት ፲ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 18, 2020)፦ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዕለታዊ ሪፖርት ይፋ መደረግ ከጀመረበት መጋቢት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. ወዲህ በ24 ሰዓት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች መገኘታቸውን የሚያመለክት ሪፖርት ዛሬ ይፋ ኾኗል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አምስት የፌዴራሊስቱ ጥምረት አባላት ታስረዋል ተባለ

Dereje Bekele

ከገለልተኛ አካል ማረጋገጫ አልተሰጠም
በሕወሓት ይመራል የተባለው ቡድን ጽሕፈት ቤቱን አዲስ አበባ ሊያደርግ ወሰነ

ኢዛ (እሁድ ግንቦት ፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 17, 2020)፦ በመቀሌ ከተማ ሊካሔድ በነበረው የኢትዮጵያ የፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት መድረክ ላይ ለመሳተፍ ወደ መቀሌ ለመሔድ ሲዘጋጁ የነበሩ የጥምረቱ አመራሮች ታስረዋል ሲል የትግራይ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ