/መሰፍን/ማርያም

የሚወለድበትን መሬት ማንም ሰው አይመርጥም፤ የዘመኑ ቅንጦት ኢትዮጵያ አርግዞ አሜሪካ መውለድ ቢሆንም፣ ልጁ ምርጫው ውስጥ የለበትም፤ አንኳን ልጁ አባትዬውም ምርጫው ውስጥ የሚገባ አይመስለኝም፤ በእንደዚህ ያለው ኢትዮጵያን አስጠልቶ -ሌላ- እንዲሆን በተፈጠረ ቅንጦት የሚወለድ ኢትዮጵያዊ ምን እንደሚሆን መተንበይ ያዳግታል፤ ልጁ ወይም ልጅቱ በራሳቸው ዝንባሌ፣ ፍላጎትና ጥረት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ግንኙነት በእልህ ከአልተለወጠ እናቶቻቸው የተለሙላቸው ማንነት ከኢትዮጵያዊነት ይገነጥላቸዋል፤ ነገር ግን የኢትዮጵያዊነት ስሜት እንዲህ በቀላሉ ተቀርፎ የሚወድቅ አይደለም፤ ሲደንቀኝ የቆየ ነገር ልናገር፤

አንድ ጊዜ በኢሰመጉ ተልእኮ ካናዳ ሄጄ አንድ ስብሰባ ላይ አንድ አርመን ወጣት ነበረ፤ ይህ ሰው ለኢትዮጵያ ያለው ስሜት በጣም የጋለ ነበር፤ በሌላ ዘመን ደግሞ ፋጡማ ሮባ በአትላንታ ማራቶን በአሸነፈች ጊዜ ደግሞ በቴክሳስ የሚኖር ከአንድ ግሪክ ገንፍሎ የወጣው ንግግር በጣምልብን የሚነካ ነበር፤ ለዚህ አርመንና ለዚህ ግሪክ የኢትዮጵያዊነት ስሜት በዘር የተላለፈላቸው አይመስለኝም፤ ስለዚህም አሜሪካ የሚወለዱትም ኢትዮጵያውያን ልጆች እናቶቻቸው ሳያውቁ ከውስጣቸው የሚያስተላልፉላቸው ስሜት ኢትዮጵያዊነታቸውን ይገነባው ይሆናል (ሙሉውን ጽሁፍ በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)

 

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ