ይሄይስ አዕምሮ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ለዘመናት ጨንፍሮ ከያዛት ድህነት ለማላቀቅ የኢህአዴግ መንግሥት የትራንስፎርሜሽን ዐዋጅ በቅርቡ ማወጁ የሚታወቅ ነው። ጥሩ መመኘት ጥሩ ነው። ዐዋጁ እንደስካሁኖቹ የግብር ይውጣና የማሞኛ ዐዋጆች ሆኖ የማይቀር ከሆነ ሀገርና ህዝብ ለሽዎች ዓመታት ተዘፍቀውበት ከነበሩበት የድህነት አዘቅትና የችግር አዙሪት መውጣታቸው ከሰይጣን በስተቀር የማያስደስተው ስለሌለ ሁላችንንም እሰየው የሚያሰኝ ዕፁብ ድንቅ ነገር ነው።

 

ይሁንና ካለፈ ልምዳችን ተነስተን ይህን አዲሱን የወያኔ መንግሥት ተምኔታዊ የሚመስል ዐዋጅም ሆነ ከዚያ በፊት በሌሎች መንግሥታት ሳይቀር ታውጀው የነበሩ የበርካታ ዐዋጆችን የመጀመሪያም ሆነ የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ ስናይ ተግባራዊነታቸውና ህዝባዊ አመኔታቸው ብዙውን ጊዜ ጥያቄ ውስጥ እንደገባ ነው። የአሁኑም ዐዋጅ፣ መንግሥት ላለፉት 19 ዓመታት ተሞኝተው ያልተሞኙለትን የኢትዮጵያን ህዝብና ”ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ” ለማዘናጋት የታለመ እስካልሆነ ድረስ ምኞታዊ ጅማሬው መልካም ነው። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ