ምነው ልዑል ሆይ! (ጎዶሊያስ)
ጎዶሊያስ
የሶሪያ ጭቁን ሕዝቦች እንደ ቅጠል ሲረግፉ፣
በጎርፍ ውሃ ውስጥ ሲጣሉ፤ በጅምላ ከምድረገጽ ሲጠፉ፣
እያረደ ሲጥለው፤ የዘር ጥላቻው ሲሰፋ፣
መተዛዘኑ ሲቀር፤ ደረት መድቃቱ በተስፋ፣
የሙት አፈር መመለሱ እየማሱ፤ እያለቀሱ በአካፋ፣ ምነው
ልዑል ሆይ፤ ምነው አምላኬ፤ ጉድ እንዲህ እየተሰማ፣
ዝምታውን አበዛኸው፤ ሶሪያ ስትሆን የሙት ባድማ።
ዓለም እንዲህ ስትታመስ፣
እምባ ሲበዛ እንደ ጎርፍ፤ እንደጠል ሲፈስ፣
እንደፋሲካ በጎች፤ እንደ ትንሳዔ ለበዓሉ፣
ወጣቱ እየታረደ፣ በጎርፍ ውሃ ውስጥ ሲጣሉ፣
ቤተክርስቲያናት ሲፈርሱ፣
የበረከት ቦታዎች እነዋልድባ ሲማሱ፣
በነጻነት መታፈን ሙስሊም ሕዝቦች ሲያለቅሱ፣
የዳውሮ ፍሬዎች ሲረግፉ፣
በተለያዩ ቦታዎች አሳፋሪ ታሪኮች ሲጻፉ፣
ምነው አምላኬ፤ ምነው ልዑል ሆይ፣
ምነው መድሕኑ፤ ምነው ዔልሻዳይ፣
ድምጽሕ ከድሃ ራቀ፤ አልሰማም አለ ተበዳይ።
ዓለም እንዲህ ስትታመስ፣
እምባ ሲበዛ እንደ ጎርፍ፤ እንደጠል ሲፈስ፣
እንደፋሲካ በጎች፤ እንደ ትንሳዔ ለበዓሉ፣
ወጣቱ እየታረደ፣ በጎርፍ ውሃ ውስጥ ሲጣሉ፣
ምነው አምላኬ፤ ምነው ልዑል ሆይ፣ ምነው
መድሕኑ፤ ምነው ዔልሻዳይ፣
ድምጽሕ ከድሃ ራቀ፤ አልሰማም አለ ተበዳይ።
የምድር ጽዋዋ ሞልቶ፣ ኃጢአት ወደ ላይ ሲፈላ፣
ቅርሻት፣ ትፋትዋ በዝቶ ፍጥረት በምድር ሲቆላ፣
ሶዶም ገሞራ ሲደገም፣ የሰላም ውሃው ሲቀየጥ በደም፤ ሲጠቁር ሲቀላ፣
ጥላቻ አይሎ፤ ፍቅር ሲጠፋ፣
ሰላም ሲርቀን፤ በቀን በይፋ፣
እምነት ሲጠፋ፤ ታርኩ ሲፈርስ፣
እምባ ሲበዛ እንደ ጎርፍ፤ እንደጠል ሲፈስ፣
እንደፋሲካ በጎች፤ እንደ ትንሳዔ ለበዓሉ፣ ወጣቱ
እየታረደ፣ በጎርፍ ውሃ ውስጥ ሲጣሉ፣ ቅዱሳን
አባቶች ከየበአታቸው ሲባረሩና፣ ሲፈናቀሉ ምነው
አምላኬ፤ ምነው ልዑል ሆይ፣
ምነው መድሕኑ፤ ምነው ዔልሻዳይ፣ ድምጽሕ
ከድሃ ራቀ፤ አልሰማም አለ ተበዳይ።
ጎዶሊያስ
1/29/13



