ልባም (ዋለልኝ እግዜር)
ዋለልኝ እግዜር
ሲሉ እየሰማሁ በጣም ይገርመኛል
በደል ተንተርሶ ህዝባችን ተኝቷል
ልሂቃን ነን ያሉም መርጠዋል ዝምታን
አይነሳም ብለው ምድር ሰማይ ቢሆን።
ተዉ እባካችሁ! ዝም አይነቅዝም ይቅር
መማር ያስፈልጋል ከተፈጥሮ ኩነት አምሳያ ቁምነገር
ስታነቃንቀው የረጋውን ኩሬ ከመሃል እስከዳር
ተስፈንጥራ ገብታ አንዲት ትንሽ ጠጠር።
ዋለልኝ እግዜር
ኅዳር 28 ቀን 2005 ዓ.ም. - ዋሺንግቶን ዲ.ሲ.



