ይኑሩ አይሙቱብን (ላቶ መለስ - አትክልት አሰፋ)
አትክልት አሰፋ
ትንሽ ይቆዩ እንጂ ጥቂት ይኑሩልን፣
ባሉበት ሰንብተው ስቃይ ተካፈሉን።
ጭንቀትን ይወቁት በሞቴ ይኑሩ፣
ይቅመሱት ባሉበት እንዲሁ እንዳሉ፤
ወደ ላይ አይሂዱ ወደሰላሙ አለም፣
እዚያ ከሄዱማ ምንም ነገር የለም፤
ወደዚያም አይሂዱ ወዲህም አይምጡ፣
ባሉበት ቦታ ላይ እዚያው ይቀመጡ
በፍትህ ፊት ቆመው በፍርድ እስኪቀጡ።
አትክልት አሰፋ
ትንሽ ይቆዩ እንጂ ጥቂት ይኑሩልን፣
ባሉበት ሰንብተው ስቃይ ተካፈሉን።
ጭንቀትን ይወቁት በሞቴ ይኑሩ፣
ይቅመሱት ባሉበት እንዲሁ እንዳሉ፤
ወደ ላይ አይሂዱ ወደሰላሙ አለም፣
እዚያ ከሄዱማ ምንም ነገር የለም፤
ወደዚያም አይሂዱ ወዲህም አይምጡ፣
ባሉበት ቦታ ላይ እዚያው ይቀመጡ
በፍትህ ፊት ቆመው በፍርድ እስኪቀጡ።