ልጅ ስምኦን ከፓሪስ

ለረፈደ ጉዞ ተነስታ ማለዳ

ሜዳ ላይ ግልቢያ ፈርሱን ወዳ

ሰክኖም አይረጋ ስሜት ከከዳ

 

ላልተቆጣ ወኔ ድንበሩን አቋርጣ

ወዳጅ ባልጠፋበት ፍለጋ ባላንጣ

 

ናርዶስ ከርቤን ሽቶ ውዶቹ ስጦታ

ቢሰጡም ለንጉስ ለንግስናው ቦታ

ልቧም ሳይሰዋ በናርዶሱ ፋንታ

ልኡሉን አገባች ሆና ልበ መንታ

 

ቃል ልሳን ፈጥሮ ለስራው ስኬት

ልሳንም ቃል ሆኖ በፍቅሩ ምህረት

ጩኸቱም በርክቶ ለነብሰ ሙላት

ሽምጥ ጋለበችው አፍላዋ ንግስት

 

ሳያት ስከተላት

ተከትዬም ሳያት

ለካስ ራሷ ናት ስሜቷ የከዳት።


ልጅ ስምኦን ከፓሪስ

 

This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ