ግርም፤ ጉርምርም!

ፍ.አ.

በሉ እናጉረምርም፤

ሞቷልም አልሞተም፤

ጤናም አለጤናም፤

ሁከት ወይም ሰላም፤

ምን ሊተረፈን ይሆን ቢመጣ ቢሄድም፤

ቢቀርም ባይቀርም ቢያልፍ ወይ ቢሽርም?

 

ይነግራል ይመክራል ቅዱሱ መጥሀፍ፤

ከውደቀት ከክስረት ወይንም ከማለፍ፤

ይቀድማል ይለናል ትእቢት በግዙፍ፤

ሰማይ ሰማይ ማየት በሁሉ መላቅ፤

አንኳሶና ዘልፎ በሁሉ መሳቅ፤

ባንቶ ፋንቶ ሁሉ መደንፋት መናቅ፤

ከፊቱ ያለውን ማሳነስ መሳለቅ፤

ይቀድማል ይለናል ሰማይ ወጥቶ ሳይወድቅ።

እውነቱን ነበረ ከጥንት የነገረ፤

ሀቅ ነው አሁንም ቃሉ አልተሻረ፤

አባት እውነቱን ነው እንድንታረም፤

ከአጉል አካሄድ ወትሮ ከመጥመም፤

መንኮትኮት ሳይመጣ ማክተሚያ ሳይቀድም።

ጉርምርም ጉርምርም፤

እንዲያው ጉርምርም፤

ታመመና ሞተ በህይወት የለም፤

እረ ጤነኛ ነው ምንም አልነካውም፤

ዝብርቅ ዝብርቅርቅርቅ እኛ አልገባንም፤

ላይደብቁት ነገር አይዶለም ዘላለም፤

ወራቱ ይቅርና ከሳምንት አያልፍም፤

እንዲያው ለነገሩ ሽረት ቢሆን ሞትም።

እኛን የገረመን የደነቀን ነገር፤

አፋፍ ላይ ተቀምጦ መደበቅ መሞከር፤

እስከዛሬ ድረስ ውርደት እንጂ ክብር፤

መዋሸት መቃዠት አያትርፍም ነበር፤

ዘንድሮ ግን እንጃ ትርፍ እያተረፈ፤

ጌዜውን ገዛና ባለበት ከነፈ፤

ረገጠ ረገጠ ጌዜውም ቀዘፈ፤

ትላንትን አለፈ፤ ዛሬን ለፈለፈ፤

ባለበት ተጓዘ ነገውን ዘረፈ።

አየ ጉን፤ አዬ ጉድ፤ ጉድ ታየ ዘንድሮ፤

በህይወት እያለ ሳይሞትም ተቀብሮ፤

አለሁ ጤና ቢለው ማነው የሚሰማው፤

ባትሞችም ሞተሻል ቀድሞ እንደተባለው፤

ግልጥ ነው ጉዳዩ ሽሽግ ነገር የለው።

እንዲው ለነገሩ ትንሽ ለማዳለቅ፤

አያገባን ነገር ቢነሳና ቢወድቅ፤

ብቻ ብቻ ብቻ ጉዳዩ ሆነና፤

ያገርና የህዝም የውስጥ የገበና፤

ነጻነት አርነት ፍትህ ልእልና፤

ይሞግተን ገባ በሞት ባለ-ገና፤

ግርም ግርም ግርም እንዴያው ጉርምርምርም፤

በህይወት!! ካለፈ!! ዳግመኛ!! አሁንም!!!!

ይህች ቀለም ሳትደርቅ ሚስጥሩ ፈንድቷል፤

ተብሎ ሊነገር አለ ወይም ሞቷል፤

እውነት ትወጣና ትዝብቱ ያፈጣል፤

ያልሆነ የሆነ እንደምን ይባላል፤

በቁሙ ሰው ሞተ፤ አልሞተም ያዋጣል?

የሞተውስ አለ ለምኑ ይበጃል?

አወየው ቀውጢ ቀን ነገ ምነ ይመጣል፤

የሞተው ተነሳ ታምር እኮ ሊባል፤

ጉርምርም ጉርምርም ነገሩ ይገርማል፤

ጉርምርም ግርምርም ነገሩ ይደንቃል።

የቸገረ ነገር የተፋ ለመላ፤

ሙሾ ወይስ ዘፈን የሀዘን?! የተድላ?!

አይቀርም ጉዳዩ ሓያ አርባም ቢባል፤

ዘጠና-ዘጠኙ እንደምን ያለቅሳል፤

ውስጡን ውስጣውስጡን ይከፋው ይሆናል፤

ደስ ቢለው ደግሞ ለምንስ ይገርማል፤

ለግራ ለቀኙም ከቶ የት ይገኛል፤

ሁሉን የሚያሰደስት ንጹህ ነው የሚባል፤

እንዲህ አይነቱማ እረ ምን ይባላልለ፤

እርግማን ነው እኢነጂ ከተራውስ ወጥቷል፤

የራሱን ጨርሶ የሌላን ይኖራል።

ግርም፤ ግርም፤ ግርም፤ ጉርምርም ጉርምርም፤

ትላንትና ማዘንም መቆጨት ማልቀስም፤

ዛሬ ሳቅ ወይ ማልቀስ ነገሩ አልገባንም፤

ሁሉም እንደፊናው የልቡን አይነግርም።

ቢሻህ ልታለቅስ ሲሻህም ልትስቅ፤

መብቱ የራስህ ነው ግናማ ተጠንቀቅ፤

የወደቀን አንሱ የሞተን አትርሱ፤

ብለው ነበር አበው ትላንት ሲቀድሱ

ለክፉም ለደጉ የት ተገኘ እርሱ፤

ታሪኩ ይውቀሰው አምላክም ይፍረደው፤

እምነት ካለው ዳነ ንስሀ ከገባው፤

ስራው ግን ፈጠጠ ሺ ጉድጓድ የገባው፤

ውሀ በልቶት ቀረ የደሞም ፍርደ አልባው።

ይዋደዱ ነበር እንደዛሬ ሳይሆን፤

ሰው አንዳማረ አይቀር ከቶ ምንም ቢሆን፤

ብሎ ነበር እርሱም ዳንኪራና ዘፈን፤

በዚያ በዘመኑ ሲጨፍር ሲዘዘፍን፤

አበው ጥበበኞች በዘመነ ሊቁ፤

አቦዬ አቦዬ አቦዬ ጻድቁ፤

ቅጠል እንዳክርማ የሚሰነጥቁ፤

ዛሬማ ቅጠሉን በቁም አደረቁ፤

ምርቃን እርግማን ይደርሳል ጠንቅቁ!!!!

ነፍስ ይማር፤ ነፍስ ይማር፤ ነፍስ ይማር፤ ከሞተም፤

የባህል ቅንነት ለሁሉም አይቀርም፤

ፍርዱ የምድረ ነው ነፍሱ ከተረፈም፤

ነገ ትመጣለች ለክፉም ለደጉም፤

ዘንባባ ለግራ ለመሀል ለቀኙም!!!!!!!!!!!!!!!


ፍ.አ. This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

 

07/23/2012 እ.ኤ.አ.

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ