አሳየዋለሁማ ሱሪዬን! (ገለታው ዘለቀ)
አሳየዋለሁማ ሱሪዬን
(ገለታው ዘለቀ በኢ-ሜይል ካሰራጨው)
ኣያ ግፈ ገፍቶ
ቢያየኝ ጊዜ
ሁኘ በትካዜ
ሆዴ ሰፊ ባህር ሁኖ
ትከሻዬ ሰፍቶ
ጫንቃዬ ደንድኖ
ቢያየኝ ጊዜ ...
ተመቸውና ጋለበኝ
አናቴ ላይ ወጥ ሰራብኝ
ስድብና ዘለፋውን
የውርደት ቃል ድፍረቱን
እየሰማሁ እንዳልሰማሁ
እያየሁኝ እንዳላየሁ
እንዲያ እንደልማዴ ተክዤ
የሆዴን በሆዴ ይዤ
አንገቴን ወደ ጉልበቴ ሰብሬ
በትግስት ሁሉን ሰፍሬ
ቢያየኝ ጊዜ ግፈ ገፊው
እንዲህ አርጎ ገመገመው
ያላዋቂ ፈሪ አረገው
ሰባ ጊዜ አጥፍቶ አይቼው
ለሱ አፍሬ ችላ ብለው
አይማርም ጃል ምንድነው?
አንግቱን እያደር አደንድኗል
ላይመለስም ምሏል
ኣይ ... እንግዲህ በቃ
ቃል ለምድር ለሰማይን
ንቆታልና ሱሪዬን
የጀግና የከት ልብሴን
ጫኑልኝማ ታጠቅ ፈረሴን
ኣይ ... በቃ በቃ በቃ
ምላሴ በጉሮሮዬ ይጣበቃ
ንቆታልና ትግስቴን
አሳየዋለሁ ሱሪየን
በቃ
(ገለታው ዘለቀ በኢ-ሜይል ካሰራጨው)



