ይሁዳ ሲፈጠር

አሥራደው (ከፈረንሣይ)

አምላክ እያወቀ ይሁዳን ሲፈጥረው፤

ልጁን እየሱስን ነበር እንዲሸጠው፤

ባይወለድ እማ ይሁዳ በዚች ምድር፤

ለክርስቶስ መሞት ማን ምክንያት ነበር?

ያዳምስ ሃጢያቱ መች ይሰረይ ነበር?!

በገባለት ቃሉ አዳምን ለማዳን፤

እንዲሸጠው ልጁን ፈጠረ ይሁዳን፤

ይሁዳን ባይፈጠር ባምላክነት እጁ፤

አብን በቸገረው እንዲሰቀል ልጁ።

በመስቀል ተሰቅሎ ክርስቶስ እንዲሞት፤

ይሁዳ እየሱስን መሳም ነበረበት፤

መሳም ያለየለት: ውሉ የጠፋበት፤

ጥላቻና ፍቅር ተደባልቀውበት።

ባይሸጥማ ኖሮ ይሁዳ እየሱስን በጥቂት ጭብጥ ብር፤

እየሱስን እየሱስ፤ ይሁዳን ይሁዳ፤ ባላልናቸው ነበር።

መልካም የፋሲካ በዓል ለሁላችን።


አሥራደው (ከፈረንሣይ)

ሚያዝያ 15/2003 ዓ.ም. (April 23 / 2011)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ