መታሰቢያነቱ (አበራ ለማ)
መታሰቢያነቱ
አበራ ለማ
በሕይወት ላለመዋደድ ተፋቅዳችሁ
የኋላ ኋላ ኋላ …
ባንዲት ጉድጓድ ታድማችሁ
የኋላ ኋላ ኋላ …
ምስጥና አፈር ላስማማችሁ
የኋላ ኋላ ኋላ …
ማንም ምንም ላይለያችሁ
የኋላ ኋላ ኋላ …
ተቃቅፋችሁ …
የኋላ ኋላ ኋላ …
ላሸለባችሁ …
ለናንተ …
ላምበሎቼ
ለጋሼ
ኃይሌ ፊዳ
ለጋሼ
ብርሀነ መስቀል ረዳ
እነሆኝ …
ይህን ያገር እዳ።
ጋዜጠኛና ደራሲ አበራ ለማ “ጥሎ ማለፍ” ለተሰኘው አዲስ መጽሐፉ መታሰቢያነት የቋጠረው ስንኝ



