ግብጥ (ዳግማዊ ዳዊት)
ግብጥ
ዳግማዊ ዳዊት
ዳውላ በአህያ - አህያ ዳውላ
ቀልቀሎ አቁማዳ - ሆነና ቱልቱላ
ግብጥ ድርቡሽ ቢባል - ደደቢት አስመራ
እስኪ ስለአባይ ስል - ማንን ልውደድ ልጥላ?
ላኪና ተላኪ - ሆናቹህ ሳላቹህ
ማንን ልውደድና - ጠላሁ ልበላቹህ?
አእምሮ የማይፈትን - ፍንትው ላለ እውነት
እንካስላንትያ - ባንባባልበት!
ዳግማዊ ዳዊት
ታህሳስ 2003 ዓ.ም.
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
ላኪና ተላኪ - ሆናቹህ ሳላቹህ 


