ያላየሁትን (ሚሊዮን ጎሣዬ)
ያላየሁትን
ሚሊዮን ጎሣዬ
እንደው ልሞክር ብዬ
ብሩሼን አዋህጄ ከሸራዬ
ላም ስዬ ብሰቅል
እንዳቅሚቲ ልሞክር
አድንቀውልኝ አጨበጨቡ
ሠዓሊው ያላየሁትን
ጥጃም አይተናል ብለው
አድናቆት ሙገሳ አበዙልኝ
ስውር ሠዓሊ አርገውኝ
ሚሊዮን ጎሣዬ
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
ከኦስሎ - ኖርዌይ



