“‘መቆያ’ ‘መቅሰስ’ ይበሉ?”

ገላነው ክራር

እርሜን እግር ጥሎኝ፣ ከ‘ነሱ አደባባይ ብወጣ፣

ጆሮ መቸስ አልሰማ አይል—“መቆያ” “መቅሰስ” ሲሉ ሰማ፤

“አልሰሜን ግባ በለው! … እሱማ ሞቶ ተቀብሮ …” አልኩታ—በሹክሹክታ—ለራሴ ብቻ—ለራሴ፣

ደ’ሞ “ይኼ የባለጌ መርዶ ነጋሪ …” ብለው ... (መቸም ለማሰር፣ መግረፍ መግደሉ፣

እንኳን ሰበብ አግኝተው፣ ሰበብ ሰርተው ማረድ ማሳረድ ያውቃሉ)

እንጂ … ከ‘ኛ ቤት — የቁርስ ምሳ ራትንም፣ ሞት ቀብራቸውንም ባረዳሁኝ፣

 

ተዝካሩን ባወጣን — በሁለት አስርት ዓመቱ፣

… በጠፋ በሞተ ቃሉ፣

‘መቆያ’ ‘መቅሰስ’ ይበሉ?

 

እኛስ አየን ሲሞቱ — ቃላቱ፣

ይብላኝ ለ‘ነሱ፣ ይህን ላልሰሙ ላላዩቱ — ለቱባ ቱባ መኳንንቱ፣

መንግሥት አስኪያጅ—ሹማሙንቱ፣

እኛ አልቅሰን በቀበርን፣ በሁለት አስርት ዓመቱ፣

 

ለነሱ ሁሌ ፋሲካ፣ ምናለ ‘መቆያ’ ‘መቅሰስ’ ቢሉ?

ከኛ ቤት፣ እንኳን ‘መቆያ መቅሰስ’፣ የቁርስ ምሳ ራትም ተፈጠመ ግብኣት መሬቱ፣

ተዝካሩ ወጣ — ሳልስቱ፣

ሊወራለት በየቤቱ—እንደ ተረት ተረቱ፣

 

እኒህ የቃላት ጥናት ጠበብት — ባለሟሉ፣

‘ቃላት ይወለዳሉ - አርጅተውም ይሞታሉ’ አሉ?

 

እነሆ ርስና ምሳ ቢሞቱ፣ ታዬ — የ‘ቁምሳ’ ልደቱ፣

ሳና ራትም መቃብር ላይ፣ ‘ምራት’ ጉብ አለ ታናቱ!

 

ቁርስ ምሳና ራትን ቁጭ ብለን ባናዋልድም፣

ቆመን አልቅሰን አቃበርን

“ቁምሳ” ና “ምራት”ን አዋለድን፣

 

አዎ! ቆመን—በሕይወት ቆመን፣

እንደ ሰው ኖረን መሞት አቅቶን፣

እንደ’ቃ ሞተን እንኖራለን!


ገላነው ክራር

This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ