መስዋዕትነትና ክብር

አበበ ንጉሤ

እዚህ ፈረንጅ ሀገር ከመጣሁ ሰነበትሁ፣

ክፉንም ደጉንም ሁሉን ተመለከትሁ።

ደሞ ጠዋት ማታ ምላሴን አርዝሜ

ከ”ላሊበላ” ይበልጥ አንደበቴን ስዬ

በእናት ሀገሬ ላይ ውግዘት አበዛለሁ

ለርኩም ሥራዎቼም ደጋፊ አብዝቻለሁ።

ሲመሽ ግን ባዶ ቤት ብቻዬን ሳስበው

ህሊና የሚሞርድ ጭንቀቴ ብዙ ነው

አስባለሁ ብዙ መዝኜ እኔነቴን

መሪ ይለዋወጣል ተከትሎ ዘመን

“ኤጭ ሀገር!” ከቶስ ምን ያስባል

ሀገር እናት ናት የማትሠራ በደል

መሪን እሷ አትሾም መሪን እሷ አትጥል

መነሳት መውደቁ የሷ ድርሻም አይደል

አዕምሮን ሰፋ አድርጐ ማየት ያስፈልጋል

እስቲ እንጠያየቅ ልባችንን አጥርተን

ለልማት ሥራዋ ምን ድጋፍ አደረግን

መከራዋን ችላ ለዚህ ለአበቃችን

“አለሁልሽ” አልናት ክንዳችን ዘርግተን?

“ኤጭ ሀገር!” ማለቱን ውግዘቱን እናስቀር

ቅድሚያ መስዋዕትነት - ፍቅርና ክብር

እንስጥ እንለግሳታ ለውድ እናት ሀገር


አበበ ንጉሤ

መስከረም 2003 ዓ.ም.

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ