ፍትህን ፍለጋ (ጌታቸው አበራ)
ፍትህን ፍለጋ
(ለአበራ የማነአብ)
ጌታቸው አበራ
(ግጥሙን በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)
ርግብ ሆነህ በረህ ...፣
አድማስን አቋርጠህ፣
ለሠላም፣ ለፍትህ፣ ለህዝብ ክብር ስትል፣
በዘምባባ ቀንበጥ ጠመንጃን ልታስጥል፣
ጠመንጃ አምላኪዎች በፍርሃት ሲርዱ፣
ያገዱህ መስሏቸው ከቆራጥ ትግልህ መስክ፣
በፈሪ ልባቸው ተናንቋቸው እልክ፣
አወረዱህ አሉ? ከርቸሌ ወህኒ ቤት፣
የነርሱ መኖሪያ መሆን ወዳለበት!
አልተረዱም እንጅ፣
ግብርህ እንደ ስምህ ደምቆ እንደአበራ፤
አላወቁም እንጅ፣ ...



