Jennife DaskalEthiopia Zare (ቅዳሜ መስከረም ፳፬-24 ቀን ፳፻፩-2001 ዓ.ም. October 4, 2008)፦ ሽብርተኝነት ለመዋጋት በሚል ምክንያት ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥታት በጥምር ኾነው ዜጎችን በእስር ቤት አጉረዋል፣ ሕገ-ወጥ ምርመራም አድርገዋል የሚል ሪፖርት ይፋ ኾነ።

 

“ሂዩማን ራይትስ ዎች” የተባለ የሰብዓዊ መብት ተንከባካቢ ቡድን ነው።በሂዮማን ራይትስ ዎች “Why Am I Still Here? The 2007 Horn of Africa Renditions and the Fate of the missing” በሚል ርዕስ የቀረበው የ54 ገጽ ሪፖርት እንደሚገልፀው፣ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ከአስር የማያንሱ የውጪ ዜጎች በሕገ-ወጥ መንገድ በእስር ቤት ታጉረው እየተሠቃዩ መሆናቸውን ገልፆ፣ ሌሎች በርካቶች ደግሞ ወዴት እንደገቡ እንደማይታወቅ አስታውቋል።

 

እ.ኤ.አ. ከ2007 ዓ.ም. ጀምሮ በሽብርተኝነት ሰበብ ከሶማሊያና ከኬንያ ተይዘው ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ እስር ቤቶች ውስጥ በርካታ እስረኞች አዲስ አበባ በሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣኖች ምርመራ ተደርጓባቸዋል በማለት ሂዮማን ራይትስ ዎች በሪፖርቱ ላይ ገልጿል።

 

በሶማሊያ የሚገኙ የእስላማዊ ፍ/ቤቶች ሕብረትን ለማስወገድ ወደ ሶማሊያ የዘለቀው የኢትዮጵያ ጦር ሞቃደሽን ከእስላማዊ ፍ/ቤቶች ነፃ በመድረግ ሀገሪትዋ በሶማሊያ ሽግግር መንግሥት እንድትተዳደር ቢያደርግም፤ በወቅቱ በተፈጠረው ግርግር በሶማሊያና በኬንያ ድንበር አካባቢ የተገኙ የበርካታ ሀገር ዜጎች በኬንያ የፀጥታ ኃይሎች ታስረው ወደ ኢትዮጵያ መጓጓዛቸውን ሪፖርቱ ይገልፃል።

 

ሪፖርቱ አሁንም ድረስ ከታሰሩት መካከል በርካቶች በኢትዮጵያ እስር ቤት መኖራቸውን ገልፆ፣ በቅርቡ የተፈቱም በእስር ወቅት የደረሰባቸው መንገላታት ከፍተኛ እንደነበረ ተጎጂዎቹን ዋቢ በማድረግ ሪፖርቱ ያትታል።

 

የሂዮማን ራይትስ ዎች 54 ገጽ ሪፖርትን ያዘጋጁት ጀኔፈር ዳስካል እንደገለፁት፣ “በደርዘኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን በምስጢራዊ መንገድ በ2007 ዓ.ም. ታስረው ጉዳያቸው ሳይታዩ በዝምታ ለረጅም ጊዜ ቆይተዋል።” ብለዋል።

 

በዚህ ምስጢራዊ እርምጃ ላይ ተሰታፊ የነበሩ የኢትዮጵያ፣ የኬንያ እና ዩናይትድ ስቴትስ መንግሥታት ከተግባራቸው እንዲታቀቡ፣ የታሳሪዎቹ ጉዳይ ሕግን የተከተለ እንዳልሆነ እና የደረሱበት ሳይታወቅ ለጠፉትም ሰዎች ጉዳይ ተጠያቂ መሆናቸውን ጀኔፌር ዳስካል ገልፀዋል።

 

እ.አ.አ. በ2006 መጨረሻ አካባቢ የቡሽ አስተዳደር የሚደግፈው የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት በሶማሊያ እስላማዊ ባለሥልጣኖች ላይ የማጥቃት ርምጃ በመውሰድ የሶማሊያን ዋና ከተማ ሞቃዲሾን ለመቆጣጠር የቻለ ቢሆንም፣ በወቅቱ ከጦርነቱ ሲሸሹ የነበሩትና በኬንያ ድንበር አካባቢ የተያዙት ከሽብርተኛ ቡድኖች ጋር ግንኙነት አላቸው በማለት ለእስር መዳረጋቸውን ሪፖርቱ አስታውቋል።

 

የኬንያ ባለሥልጣናት በትንሹ ከ150 የማያንሱ ወንዶችን፣ ሴቶችን እና ሕፃናት ያሰሩ ሲሆን፣ ታሳሪዎቹ የዩናይትድ ስቴትስን፣ ዩናይትድ ኪንግደምና የካናዳ ዜጎችን ጨምሮ የ18 ሀገር ዜጎች መሆናቸውን ይፋ አድርጓል።

 

እ.አ.አ. ከጥር እስከ የካቲት 2007 ድረስ የኬንያ መንግሥት በደርዘኖች የሚቆጠሩትን ለእስር ቢዳርግም፣ ጉዳዩን ለቤተሰቦቻቸው ሳያስታውቅ፣ እስረኞቹ ጠበቃ ሳያቆም ወደ ሶማሊያ በመጓጓዝ በመጨረሻም ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፈው መሰጠታቸውን ገልፆ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ከሶማሊያ ማሰሩን አጋልጧል።

 

በመጨረሻም ታሳሪዎቹ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች በማጓጓዝ የደረሱበት ሊታወቅ አለመቻሉን ጠቅሷል። የእስረኞቹን ጉዳይ ለኤምባሲያቸው ባለማሳወቅ፣ በመሸፋፈን እና በመካድ፣ ቤተሰቦቻቸው እንዳይጎበኝዋቸው በማድረግ እና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተንከባካቢ ቡድኖች ጉዳዩን መከታተል እንዳይችሉ ተደርጓል ይላል ሂዩማን ራይትስ ዎች በዘገባው። ቁጥራቸው በግልፅ ያልታወቁ እስረኞች በዩናይትድ ስቴትስ የፀጥታ ኤጀንሲ (CIA) እና በፌዴራል የምርመራ ቢሮ (FBI) በአዲስ አበባ ምርምራ ተደርጓባቸዋል በማለት ሪፖርቱ ገልጿል።

 

“እ.ኤ.አ. ከየካቲት 2007 ጀምሮ የኢትዮጵያ የፀጥታ ሠራተኞች በየቀኑ እስረኞቹን ከታሰሩበት ቦታ በማጓጓዝ (ከታሳሪዎቹ መካከል እርጉዝ ሴቶችም ይገኛሉ) አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ ቪላዎች ውስጥ በዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣኖች ከሽብርተኝነት ጋር ባላቸው ግኑኝነት ዙሪያ ተደጋጋሚ ምርምር ሲደረግባቸው ቆይቶ፣ አመሻሽ ላይ የኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች እስረኞቹን ወደ ታሰሩበት ይመልሷቸዋል።” ይላል ሪፖርቱ።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ