Derg AuthoritiesEthiopia Zare (ዓርብ መስከረም ፪ (2) ቀን ፳፻፩ (2001) ዓ.ም. September 12, 2008)፦ ባለፈው ዓመት ግንቦት 18 ቀን 2000 ዓ.ም. የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኮ/ል መንግሥቱ ኃይለማርያምን ጨምሮ በሃያ የደርግ ባለሥልጣናት ላይ የሞት ፈርዶባቸው የነበረ ሲሆን፣ አሁን በእስር ላይ የሚገኙትና ሞት የተፈረደባቸው የደርግ ባለሥልጣናት ቅጣታቸው ወደ ዕድሜ ልክ እንዲቀየርላቸው ለማድረግ የሀገር ሽማግሌዎች ጥረት መጀመራቸውን ምንጮች ጠቆሙ።

 

ምንጮቻችን እንደጠቆሙት አቶ ዳዊት የተባሉ ግለሰብ የአገር ሽማግሌዎች ሰብሳቢ የሆኑትን ፕሮፌሠር ኤፍሬም ይስሓቅን እና ወ/ሮ ጽዮን አንዶምን በማስተባበር ከተቻለ ከእስር የሚለቀቁበትን ካልተቻለ ደግሞ እስሩ ወደ ዕድሜ ልክ የሚቀየርበትን ለማመቻቸት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ላይ እንደሆኑ ገልጸዋል።

 

ነገር ግን በሞት እንዲቀጣ የተወሰነበት ሰው የፕሬዝዳንቱን ምህረት ማግኘት የሚችለው ወደ ዕድሜ ልክ ዝቅ ሊል በሚችል ቅጣት በመሆኑ፣ ጉዳዩ ፕሬዝዳንቱ ዘንድ መቅረቡን ምንጮች ጠቁመዋል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ