* አወዛጋቢው ሮበርት ሙጋቤ ዳግም ለምርጫ እወዳደራለሁ አሉ

Robert Mugabeየ92 ዓመቱ አዛውንት በቀጣይ ምርጫ ተወዳድሬ በፕሬዝዳንትነት እቀጥላለሁ ብለዋል። ፓርቲያቸውም እንደሚፈልጋቸው ተናግረዋል። ከሁለት ሳምንታት በፊት ባለቤታቸውን ወደ ወንበራቸው ለማምጣት እያዘጋጇቸው እንደነበረ መዘገቡ አይዘነጋም። ሮበርት ሙጋቤ ሞት አይደፍረኝም ለረዥም ዓመታት እኖራለሁ ብለው መናገራቸው ይታወቃል።

* በጋምቢያ የምርጫ ፍጥጫው ተባብሷል

አገሪቱ ከሁለት ሳምንት በፊት ባካሄደችው ምርጫ የተሸነፉት ፕሬዝዳንቱ ያህያ ጃሜይ የምርጫ ውጤቱን አሜን ብለው መቀበላችውን በመግለጽ የምርጫ ሥርዓቱም ፍጹም ተአማኒና ስህተት ያልታየበት ብለው አሞካሽተው ነበር። ይሁንና ግን በዚህ ሳምንት መግቢያ ላይ ቃላቸውን በማጠፍ ምርጫው በመጭበርበሩ ውጤቱን አልቀበልም በማለት ተናግረዋል። በዚህም ብቻ ሳያበቁ የምርጫ ቦርዱን ጽሕፈት ቤት በወታደር በማስከበብ ሠራተኞቹ እንዳይገቡ አግደዋል። ዳግም ምርጫ እንዲካሄድም ጥሪ አቅርበዋል።

* የደቡብ ሱዳኑ የሽምቅ ተዋጊ መሪ ሬክ ማቻር በደቡብ አፍሪካ በቁም እስር ላይ ናቸው

የደቡብ ሱዳኑ የሽምቅ ተዋጊ መሪ ሬክ ማቻር በደቡብ አፍሪካ በቁም እስር ላይ መሆናቸው የተነገረውም በዚህ ሳምንት ነው። ሬክ ማቻር ደቡብ አፍሪካ የተጓዙት ለሕክምና ሲሆን፣ ሕክምናቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ነው ምንም አይነት እንስቃሴ እንዳያደርጉ እገዳ የተጣለባቸው። እንደ አገር ከቆመች ገና አምስት ዓመት ያላስቆጠረችው ደቡብ ሱዳን ወደ እርስ በእርስ ጦርነት ስትገባ ሦስተኛ ዓመቷ ሲሆን፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች መገደላቸውና ሌላ ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ቄያቸውን ጥለው ተሰደዋል። ጋብ ብሎ የነበረው ጦርነት ባለፈው ሐምሌ ዳግም ሲያገረሽ በምክትል ፕሬዝዳንትነት ተሹመው የነበሩት ሬክ ማቻር አገር ጥለው ለመሰደድ ተገደዋል።

* የአሜሪካው ምክትል ሰክሬታሪ ወደ ኢትዮጵያ አቀኑ

የአሜሪካው ምክትል ሰክሬታሪም ወደ ኢትዮጵያ ያቀኑት በዚህ ሳምንት ውስጥ ነው። ባለሥልጣኑ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጉዳይ ላይ ሰፊ ውይይት ያደርጋሉ ነው የተባለው። ይሁንና ግን ትናንት ኅሙስ ዲሴምበር 15 ቀን 2016፣ የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው እያደረጓቸው ያሉት ውይይት ብዙም እንዳልጣሟቸው ነው። በዚህም ሳቢያ ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ ለጋዜጠኞች ይሰጣሉ ተብሎ የተያዘላቸውን መግለጫ ሰርዘዋል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ