US asst. secretary Malinowski

ኢትዮጵያ ዛሬ (ማክሰኞ ታህሳስ ፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 13, 2016)፦ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየውን ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ተከትሎ የአሜሪካ ምክትል ሰክሬታሪ የሆኑት ሚስተር ማሊኖቭስኪ ወደ አዲስ አበባ እንደሚያቀኑ የአገሪቱ ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

የሚስተር ማሊኖቭስኪ የኢትዮጵያ ጉዞ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት የካቲት ወር ላይም ተመሳሳይ ጉብኝት አድርገው ነበር።

ባለሥልጣኑ ከነገ ጀምሮ ለአራት ቀን የሥራ ጉብኝት የሚያደርጉ ሲሆን፣ ሀገሪቱ አሁን የገባችበትን የፖለቲካ ማጥ ተንተርሶ ከመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ ተቋማት መሪዎች ጋር ይወያያሉ ተብሏል።

ላለለፉት በርካታ ወራት አሜሪካ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የሕግ የበላይነት መጓደል እንደሚያሳስባት በተደጋጋሚ ስትገልጽ ቆይታለች። ከሰሞኑም ዜጎቿ ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉዞ እንዲያራዝሙ ወይም ከፍተኛ ጥንቃቄ የተሞላበት እንዲያደርጉ አሳስባለች።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ