Ethiopia Zare (እሁድ ነኀሴ 4 ቀን 2000 ዓ.ም. August 10, 2008)፦ በደቡብ ክልል በቡታጅራ ከተማ በጉራጌ ዞን በሚገኙ ሁለት ወረዳዎች ስያሜ አሰጣጣጥ ጋር በተያያዘ በነዋሪዎችና በፖሊስ መካከል በተነሳ ግጭት አራት ሰው ሲቆስሉ፣ 12 ሰዎች መታሰራቸው ታስረዋል።

 

የደቡብ ክልል ምክር ቤት በ1995 ዓ.ም. "ዱቢ" የተባለ አንድ ቀበሌ ያለው ወረዳና "መስቃን" የተባለ 41 ቀበሌዎች ያሉት ወረዳ በአንድ ላይ ተቀላቅለው "ዱቢ መስቃን" በሚል እንዲጠሩ ተወስኖ ነበር። የወረዳው ባለሥልጣናት ጉዳዩን በሚመለከት በተደጋጋሚ ስብሰባ በመጥራት ሲያወያዩ ከቆዩ በኋላ በመጨረሻ ለአምስት ዓመታት ተግባራዊ ያልተደረገው ውሳኔ ከዚህ በኋላ ተግባራዊ እንደሚደረግ የሚገልጽ ቀጭን ትዕዛዝ በማስተላለፋቸው ረብሻው የተቀሰቀሰ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ያስረዳሉ።

 

በረብሻው በተደረገ የተኩስ ልውውጥ አራት ሰዎች ሲቆስሉ የ13 ወረዳ የምክር ቤት አባላትና የከተማው ባለሥልጣኖች ቤት ንብረት ተዘርፏል፣ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ተሰባብረዋል። ከተማዋም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውላለች። 12 ሰዎች መታሰራቸውን ለመረዳት ችለናል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ