ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እጅግ ታሟል

ኢትዮጵያ ዛሬ (ማክሰኞ ታህሳስ ፲፰ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 27, 2016)፦ ሰሞኑን ያለበት ባለመታወቁና እስር ቤቶቹ ሁሉ ”አናውቅም” በማለታቸው ቤተሰቦቹን ጨምሮ ጉዳዩ ብዙዎችን አስጨንቆ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ በመጨረሻ ዝዋይ እስር ቤት ቢገኝም፤ በአሁኑ ሰዓት እጅግ ታምሞ ሆስፒታል መግባቱ ታወቀ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢትዮጵያ ዛሬ (ማክሰኞ ታህሳስ ፲፰ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 27, 2016)፦ ሰሞኑን ያለበት ባለመታወቁና እስር ቤቶቹ ሁሉ ”አናውቅም” በማለታቸው ቤተሰቦቹን ጨምሮ ጉዳዩ ብዙዎችን አስጨንቆ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ በመጨረሻ ዝዋይ እስር ቤት ቢገኝም፤ በአሁኑ ሰዓት እጅግ ታምሞ ሆስፒታል መግባቱ ታወቀ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢትዮጵያ ዛሬ (ሰኞ ታህሳስ ፲፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 26, 2016)፦ ባለፈው ኅሙስ ታህሳስ ፲፬ ቀን ፳፻፱ (Dec. 22, 2016) በሰባ ሁለት ዓመቱ ሕይወቱ ያለፈችው፣ የጀግናው አትሌት ሻምበል ምሩጽ ይፍጠር የጸሎተ ፍትሐቱ ሥነሥርዓት ነገ ማክሰኞ ታህሳስ ፲፰ ቀን (Dec. 27) ጠዋት አምስት ሰዓት ላይ ቶሮንቶ ካናዳ በሚገኘው ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ የደረሳት ዘገባ አስረዳ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢትዮጵያ ዛሬ (ረቡዕ ታህሳስ 5 ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 14, 2016)፦ ላለፉት ስምንት ተከታታይ ቀናት ቤተሰቦቹ በአገሪቱ ውስጥ ባሉ ወህኒ ቤቶች ሁሉ ዞረው ሲፈልጉ ሰንብተዋል። አቤቱታቸውንም ለሚመለከተው ክፍል አሰምተዋል። ይሁን እንጂ ተመስገንን አየሁ የሚል አንድም የወህኒ ቤት አስተዳዳሪ አልተገኘም።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢትዮጵያ ዛሬ (ማክሰኞ ታህሳስ ፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 13, 2016)፦ የሰባት ኢትዮጵያውያን አስከሬን በታንዛኒያ ወንዝ ውስጥ ተጥሎ መገኘቱን የአገሪቱ መንሥግት አስታወቀ። ኢትዮጵያውያኑ ወንዝ ውስጥ ሆን ተብለው የተጨመሩ መሆኑንም ፖሊስ ተናግሯል። አስከሬኖቹ በጆኒያ ከአሸዋ ጋር ተደርገው ነው ወደ ወንዝ የተወረወሩት ሲል ፖሊስ መግለጡን የኬንያ ቴሌቭዥኖች የዘገቡ ሲሆን፣ ሟቾቹ በሙሉ ወንዶች መሆናቸው ታውቋል።

ኢትዮጵያ ዛሬ (ማክሰኞ ታህሳስ ፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 13, 2016)፦ በየዓመቱ በመላው ዓለም በሥራቸው ሳቢያ ብቻ ወደ ወህኒ ቤቶች የተወረወሩ ጋዜጠኞችን ቁጥርና ስም ዝርዝር ይፋ የሚያወጣው ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪው ድርጅት ሲፒጄ፤ ዛሬ ባወጣው ሪፖርት በኢትዮጵያ ወህኒ ቤቶች 16 ጋዜጠኞች መታጎራቸውን ይፋ አድርጓል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
አብርሃም ቀጄላ
የፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ”የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ” አዲስ መጽሐፍ በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ሦስት ከተሞች ተመረቀ። በሦስት ተከታታይ ቀናት ከዲሴምበር ፫ ቀን ጀምሮ በቨርጂኒያ፣ በዋሽንግተን ዲሲ እና በሜሪላንድ በሚገኙ የኢትዮጵያውያን ሬስቶራንቶች ነው ምርቃቱ የተካሄደው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢትዮጵያ ዛሬ (ቅዳሜ ታህሳስ ፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 10, 2016)፦ ባለፈው ሣምንት በምርጫ መሸነፋቸውን በፀጋ መቀበላቸውን አሳውቀው የነበሩትና ጋምቢያን ላለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት የመሩት የጋምቢያው ፕሬዝዳንት ያህያ ጃሜይ፤ በዛሬው ዕለት የምርጫውን ውጤት አልቀበልም አሉ። ድጋሚ ምርጫ መካሄድ አለበት ማለታቸው ተደመጠ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢትዮጵያ ዛሬ (ቅዳሜ ታህሳስ ፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 10, 2016)፦ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ባለፈው ክረምት በሪዮ ዲጄኔሮ ኦሎምፒክ ማራቶን ውድድር ላይ የብር ሜዳሊያ ከመቀዳጀቱም በላይ በአገሩ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመቃወም እጆቹን አጣምሮ በዓለም አደባባይ ላይ ካሳየ ወዲ የመጀመሪያው የሆነውን ውድድር ሊያደርግ በዝግጅት ላይ ነው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢትዮጵያ ዛሬ (ዓርብ ኅዳር ፴ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 9, 2016)፦ “ተመስገን ያለበትን ቦታ ለማወቅ ለ3ኛ ቀን ፍለጋ አንዳችን ወደ ዝዋይ፣ አንዳችን ወደ ሸዋ ሮቢት፣ አንዳችን ወደ ማዕከላዊ እስር ቤቶች እየሄደን ሲሆን፤ እናታችን ደግሞ ወደ ቤተክርስቲያን እየሄደች ነው።” ሲል ዛሬ ጠዋት የጋዜጠኛ ተመስገን ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ በፌስቡክ ገጹ ቤተሰቡ ያለበትን ኹናቴ እና ያደረበትን ስጋት ገለጠ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢትዮጵያ ዛሬ (ዓርብ ኅዳር ፴ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 9, 2016)፦ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ብሎም ከ1981 እስከ 1983 ዓ.ም. በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ኢትዮጵያን ያገለገሉት አቶ ተስፋዬ ዲንቃ ያዴሳ ኅዳር ፳፱ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. በ፸፯ ዓመታቸው አረፉ።