አቶ ሀብታሙ አያሌው ወደ ውጭ ሔዶ ሊታከም ነው

Habtamu with his daughter

(ቢቢኤን) ባለፈው ዓርብ ኅዳር 23 ቀን 2009 ዓ.ም. ከተከሰሰበት የሽብር ክስ በነጻ የተሰናበተው አቶ ሀብታሙ አያሌው ወደ ውጭ ሔዶ እንደሚታከም ገለጸ። የቀድሞ አንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረው አቶ ሀብታሙ፣ ሆሞሮይድ በተባለ በሽታ በጽኑ ሲታመም እንደሰነበተ ይታወቃል። ውጭ ወጥቶ ለመታከም በተደጋጋሚ ለፍርድ ቤት አመልክቶ በተለያዩ ሰበቦች ማመልከቻው ውድቅ ሲደረግበት የቆየው አቶ ሀብታሙ፣ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ነጻ መባሉን ተከትሎ ውጭ ሔዶ ለመታከም ማቀዱን አስታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንኮበር ከተማ በፎቶ ለታሪክ ማስታወሻነት ተቀመጠች

Photographer Michael Tsegaye

ኢትዮጵያ ዛሬ (ኀሙስ ኅዳር ፳፱ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 8, 2016)፦ የኢትዮጵያዊው ፎቶግራፈር ሚካኤል ፀጋዬ፤ አጤ ምኒልክ በዋና ከተማነት የቆረቆርዋትን ”አንኮበር”ን ለወደፊት ለታሪክ ማስታወሻ በፎቶግራፍ ለማስቀመጥ በማሰብ ከአስር ዓመት በፊት ያነሳቸውን ፎቶግራፎች በኤግዚቢሽን አቀረበ። ኢግዚቢሽኑ በአዲስ ፋይን አርት ጋለሪ ከኖቨምበር ፲፱ እስከ ጃንዋሪ ፳፩ ክፍት ሆኖ ይቆያል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

”ፕ/ር መረራን ያሰርኩት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ስለጣሱ ነው” ኮማንድ ፖስቱ

Prof. Merera Gudina

ኢትዮጵያ ዛሬ (እሁድ ኅዳር ፳፭ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 4, 2016)፦ ፕ/ር መረራ ጉዲና ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ከፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር በቤልጅየም ብራስልስ ”ተገናኝተው በመውያየታቸውና መግለጫ በመስጠታቸው” ነው ያሰርኳቸው ሲል ኮማንድ ፖስቱ ገለጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አትሌት አልማዝ አያና የዓመቱ የዓለም ምርጥ አትሌት ተብላ ተመረጠች

Almaz Ayana and Husain Bolt

ኢትዮጵያ ዛሬ (ቅዳሜ ኅዳር ፳፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 3, 2016)፦ ዓለማቀፉ የአትሌቲክስ ማኅበር ፌደሬሽን ኢትዮጵያዊቷን የ10 ሺህ ሜትር ሪኮርድ ባለቤት አልማዝ አያናን የ2016 የዓለም ምርጥ አትሌት በማለት ትናንት ማምሻውን የሸለማት ሲሆን፣ ከወንዶ ትሌቶች ደግሞ ጃማይካዊው የአጭር ርቀት ሯጭ ዩሴን ቦልት ተሸላሚ ሆኗል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፕ/ር መረራ ጉዲና አዲስ አበባ ሲገቡ ታሰሩ

የታሰሩት በአውሮፓ ሕብረት ባደረጉት ንግግር እና ከፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር በመታየታቸው ይሆናል ተብሎ ይገመታል

Prof. Merera Gudina

ኢትዮጵያ ዛሬ (ረቡዕ ኅዳር ፳፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 30, 2016)፦ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር የሆኑት ፕ/ር መረራ ጉዲና መታሰራቸው ተጠቆመ። ፕ/ር መረራ የታሰሩበት ምክንያት ለጊዜው በትክክል ባይታወቅም፤ በአውሮፓ ሕብረት ተገኝተው ባደረጉት ንግግርና ከፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር በመታየታቸው ሊሆን ይችላል ተብሎ ይጠረጠራል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሹም ሽሩ ሥልጣናቸውን ያጡ የኢህአዴግ ጎምቱ ባለሥልጣናት የሙሉ አምባሳደርነት ሹመት ተሰጣቸው

ከ፲፯ (17) ቀን በኋላ አዲስ ሥልጣን ተሰጣቸው

Ato Tsegaye Berhe, Ato Redwan Hussen, W/o Zenebu Tadesse, and Ato Tolossa Shagie

ኢትዮጵያ ዛሬ (ቅዳሜ ኅዳር ፲ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 19, 2016)፦ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ባለፈው ሹም ሽር ሥልጣናቸውን ላጡ ስምንት የኢህአዴግ የቀድሞ ባለሥልጣናት የሙሉ አምባሳደርነት ሹመት ሰጡ። እነኝህ የኢህአዴግ ጎምቱ ባለሥልጣናት የሙሉ አምባሳደርነት ሹመት እንደተሰጣቸው የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ቢገልጽም፤ በየትኞቹ አገሮች ላይ ሹመት እንደተሰጣቸው አልገለጸም፤ ተሰናባቾቹ አምባሳደሮችም አልታወቁም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዮናታን ተስፋዬ ቀንና ሌሊት በሰንሰለት እንደሚታሰር ተዘገበ

Ato Yonatan Tesfaye(ኢሰመፕ) ፌስቡክ ላይ በጻፋቸው ጹሁፎች ምክንያት የሽብር ክስ ቀርቦበት ጉዳዩ በፍ/ቤት እየታየ የሚገኘውና በእስር ቂሊንጦ ያለው የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ በሚገኝበት እስር ቤት ውስጥ ከአርብ ኅዳር 2/2009 ዓ.ም. ጀምሮ ቀንና ሌሊት በሰንሰለት ታስሮ እንደሚገኝ ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ