ጃዋር መሐመድና አደጋውን ያደረሱ ግለሰቦች ለፍርድ እንዲቀርቡ ኢዜማ ጠየቀ

EZEMA

“ተከብቤአለሁ” በማለት ለደረሰው ጥፋት መነሻ ከኾነው ግለሰብ ጀምሮ አደጋ ያደረሱት በሙሉ ለፍርድ ይቅረቡ! (ኢዜማ)

ኢዛ (ማክሰኞ ጥቅምት ፲፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 29, 2019)፦ በአገር መረጋጋት፣ ሰላም፣ እንዲሁም ከቀጣሁ ምርጫ ጋር ተያይዞ ባሉ አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ ውይይት በፍጥነት መጀመር እንዳለበት ኢዜማ አሳሰበ። ለሰሞኑ ብጥብጥ፣ የዜጎች ሕይወት መጥፋትና ንብረት መውደም መነሻ ከኾነው ከጃዋር ጀምሮ አደጋው ያደረሱት በሙሉ ለፍርድ ይቅረቡ ሲል ኢዜማ ጠይቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጠቅላይ ሚንስትሩ በሰሞኑ ክስተት ከሩሥያ መልስ መግለጫ ሠጡ

ጃዋር መሐመድ

ይህ ሁሉ ለምን እንደመጣብን እናውቃለን፤ ከዚህ የበለጠ ፈተና ቢያጋጥመንም እንኳን የጀመርነውን ጉዞ አናቋርጥም

ኢዛ (ቅዳሜ ጥቅምት ፲፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 26, 2019)፦ ሰሞኑን በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች በተፈጠረው እጅግ አሳዛኝ ድርጊቶችን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ማምሻውን መግለጫ ሠጥተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጃዋርን “ተከብቤአለሁ” የፌስ ቡክ መልእክት ተከትሎ አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ሐረርና ሌሎች ከተሞች ታምሰው ዋሉ

Young men joined the protest at Jawar's house in the capital Addis Ababa

በአዳማና በሐረር የሰዎች ሕይወት ተቀጠፈ፣ ንብረትም ወደመ

ኢዛ (ረቡዕ ጥቅምት ፲፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 23, 2019)፦ በአዲስ አበባ፣ በአንዳንድ የኦሮሚያ ክልል ከተሞችና በሐረር ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም. የተረጋጋ እንቅስቃሴዎችን የሚፈታተን ድባብ ያጠላበት ከመኾኑንም በላይ የሰው ሕይወት የቀጠፈና በንብረት ላይ ውድመት የፈጠረ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

PM Dr Abiy Ahmed's book, Medemer

“መደመር” መጽሐፍ የኢሕአዴግን የወደፊት አቅጣጫ ይጠቁማል

ኢዛ (ዓርብ ጥቅምት ፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 19, 2019):- ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ “መደመር” የሚል ርዕስ የተፃፈውና ቀጣዩን የአገሪቱን አቅጣጫ የሚያመላክቱ ትንተናዎችን ያካተተው ነው የተባለው መጽሐፍ ዛሬ በይፋ ተመርቆ ለገበያ ይቀርባል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢሕአዴግ ሕወሓት ላይ መግለጫ አወጣ

EPRDF press release on TPLF

“ኢሕአዴግን ከግንባርነት ወደ ውሕድ ፓርቲ የማሸጋገር ጉዳይ ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ ሲነሳ የቆየ ጥያቄ ነው” ኢሕአዴግ

ኢዛ (ዓርብ ጥቅምት ፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 18, 2019):- ኢሕአዴግን ውሕድ ፓርቲ ለማድረግ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ላይ መድረሱ እየተገለፀ ባለበት ወቅት፤ ሕወሓት ውሕደቱን እንደማይቀበልና ከዚሁ ጋር አያይዞ ያወጣው መግለጫ የፓርቲውን አሠራር የጣሰ መኾኑን የኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኦዴፓ “ኢሕአዴግ ሲያራምደው የነበረው አብዮታዊ ዴሞክራሲ በቃው!” አለ

TPLF and ODP

ለሕወሓትና ለአብዮታዊ ዴሞክራሲያውያን የተሰጠ መግለጫ

ኢዛ (ዓርብ ጥቅምት ፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 18, 2019):- የኢሕአዴግ አወቃቀር ሲመራበት የነበረው አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሕዝብን ውሳኔ ሰጪነት የሚገድብ ስለኾነ ለደረስንበት የትግል መድረክ የሚመጥን አለመኾኑን የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአማራ ክልል የፀጥታ ስጋት ባለባቸው ቦታዎች የፌዴራል መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ፈቀደ

Amhara region

“አሁን ያለው ሁኔታ ለክልሉም ኾነ ለመላው አገሪቱ የፀጥታ ስጋት ወደመኾን ተሸጋግሯል” የደኅንነትና የፀጥታ ካውንስሉ

ኢዛ (ሐሙስ ጥቅምት ፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 17, 2019):- ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ በቅማንት ብሔረሰብ ማንነት ጥያቄና በተያያዙ ምክንያቶች የሚታየውን የፀጥታ መደፍረስ ለማረጋጋት፤ የፌዴራል መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ መወሰኑንና በአካባቢው ያለውን የፀጥታ ችግር አስመልክቶ የአማራ ክልል ደኅንነትና የፀጥታ ካውንስል የጋራ ውሳኔ አሳልፏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጠንካራ ውሳኔ ያሳልፍበታል የተባለውን ስብሰባ ጀመረ

Lemma Megerssa honouring Abiy Ahmed

ለሕወሓትም ምላሽ የሚሠጥበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል

ኢዛ (ረቡዕ ጥቅምት ፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 16, 2019):- በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዛሬ ጥቅምት 5 ቀን 2012 ዓ.ም. መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል። ስብሰባው በወቅታዊው ክልላዊና አገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚመክር ሲሆን፣ የተለያዩ ውሳኔዎች የሚተላለፉበትና ለሕወሓትም ምላሽ የሚሠጥበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሕወሓት ከውሕደቱ ውጭ ነኝ አለ

TPLF press release

“በውሕደት ስም በፍጹም ፀረ-ዴሞክራሲያዊ መንገድ አዲስ አሃዳዊ ድርጅት ሊመሰረት አይገባም” ሕወሓት

ኢዛ (ማክሰኞ ጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 15, 2019):- ኢሕአዴግን ወደ አንድ ውሕድ ፓርቲ ለማምጣት እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ የማይቀበል መኾኑን ሕወሓት በይፋ አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እነብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ዛሬ በ10 ሺህ ብር ዋስ ተለቀቁ

BG Tefera Mamo and Col. Alebel Amare

ኢዛ (ሰኞ ጥቅምት ፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 14, 2019):- ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በባህር ዳር ከተማ በአማራ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ግድያና “መፈንቅለ መንግሥት” ጋር ተያይዞ ተጠርጥረው በእስር ላይ የነበሩት እነብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 3 ቀን 2012 ዓ.ም. በ10 ሺህ ብር ዋስትና ተለቀቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ