በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ሰዎች ቁጥር 11 መድረሱን ስዊድን አስታወቀች
በዛሬው ዕለት አራት፣ ትናንት ደግሞ አምስት ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል ተባለ
ኢዛ (ዓርብ የካቲት ፳ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 28, 2020)፦ በዛሬው ዕለት አራት ሰዎች በሦስት የተለያዩ ከተሞች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የስዊድን መገናኛ ብዙኀን ዘገቡ። በትናንትናው ዕለት ደግሞ አምስት ሰዎች፣ ከትናንት በስቲያ አንድ፣ ከሳምንታት በፊት አንድ ሰው በቫይረሱ የተያዙ መኖራቸው ታውቋል። እስካሁን በስዊድን በቫይረሱ የተያዙት ቁጥር አስራ አንድ ደርሷል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...



