የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ምርጫ ጉዳይ ውሳኔ ያሳልፋል ተባለ
ክልሉ ምርጫውን የሚከለክለኝ የለም ብሏል
ኢዛ (ረቡዕ ሐምሌ ፳፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 5, 2020)፦ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል ከሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ ውጭ ምርጫን ለማድረግ የሚገፋበት ከኾነ በቅርቡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በመሰብሰብ ውሳኔ ሊያሳልፍ ይችላል ተብሏል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢዛ (ረቡዕ ሐምሌ ፳፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 5, 2020)፦ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል ከሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ ውጭ ምርጫን ለማድረግ የሚገፋበት ከኾነ በቅርቡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በመሰብሰብ ውሳኔ ሊያሳልፍ ይችላል ተብሏል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢዛ (ሐሙስ ሐምሌ ፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 9, 2020)፦ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋ እና አመራሮችን መታሰር ተከትሎ ፓርቲው ባወጣው መግለጫ፤ ሰሞኑን ጽንፈኞች በቀሰቀሱት አመጽ ለደረሰው እልቂትና ንብረት ውድመት የአንድ ቀን ጀንበር የወለደው ችግር አለመኾኑን ገለጸ። ፓርቲው የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በአገሪቱ እየታየ ለሚገኘው ሥርዓት አልበኝነትና ሲልም ሽብርተኛነት ቀጥተኛ ተጠያቂዎች እንደሆኑ አበክሮ እንደሚያምን በመግለጫው አሳውቋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢዛ (ማክሰኞ ሰኔ ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 7, 2020)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር ተገናኝተው በበጀት ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ይሰጣሉ። በወቅታዊ ጉዳዮችና የአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተከሰተው ኹከት፣ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት ጋር በተያያዘም ማብራሪያ እንደሚሰጡ ተገምቷል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢዛ (ሰኞ ሰኔ ፳፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 6, 2020)፦ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ዛሬ ሰኞ ሰኔ 29 ቀን በሊቀመንበሩ በአቶ በለጠ ሞላ አማካኝነት በሰጠው መግለጫ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሕወሓት የሠጠውን የፓርቲ ምዝገባ ሰርቲፊኬት እንዲሰርዝ ጥያቄ አቀረበ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢዛ (ሰኞ ሰኔ ፳፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 6, 2020)፦ ከአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ በተቀሰቀሰው ኹከትና የበርካቶችን ሕይወት ካጠፋው ጉዳይ ጋር ተያይዞ የትግራይ ቲቪ እና ድምፂ ወያኔ ከሳተላይት እንዲወርዱ መንግሥት ማድረጉ ታወቀ። በአገር ቤት ሥርጭታቸውን ለማቆም ተገድደዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢዛ (እሁድ ሰኔ ፳፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 5, 2020)፦ ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ ውኃ ለመሙላት የሚያስችላትን ግንባታ መጨረስዋንና የውኃ መሙላት ሒደቱን እንደምትጀምር የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂንየር ስለሺ በቀለ ገለጹ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢዛ (ሐሙስ ሰኔ ፳፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 2, 2020)፦ አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ የአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ለበርካቶች ሞት ምክንያት የኾነውን ኹከት በመቀስቀስ እና በሰው ሕይወት ማጥፋት ተጠርጥረው ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 25 ቀን 2012 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀረቡ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢዛ (ሐሙስ ሰኔ ፳፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 2, 2020)፦ ባለፈው ሰኞ በተተኮሰበት ጥይት ሕይወቱ ያለፈው የታዋቂው የኦሮምኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ የአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 25 ቀን 2012 ዓ.ም. በተወለደበት አምቦ ከተማ በሚገኘው ገዳመ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያ ተፈጸመ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢዛ (ሐሙስ ሰኔ ፳፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 2, 2020)፦ በአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተጠርጥረው የተያዙት ሦስት ሰዎች ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 25 ቀን 2012 ዓ.ም. ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ ከተጠርጣሪዎቹ አንዷ ሴት ነች።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢዛ (ረቡዕ ሰኔ ፳፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 1, 2020)፦ የአርቲትስት ሐጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በአዲስ አበባና በተለይም በኦሮሚያ ክልል በርካቶች እየታሰሩ ሲሆን፣ ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 24 ቀን በአዲስ አበባ ከታሰሩት ውስጥ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋ መታሰሩ ተገለጸ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...