ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ራሳቸውን አገለሉ

Dr. Tedros Adhanom

ከአንድ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ተገናኝተው ነበር

ኢዛ (ሰኞ ጥቅምት ፳፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 2, 2020)፦ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድኃኖም በኮሮና ቫይረስ ከተያዘ አንድ ግለሰብ ጋር መገናኘታቸውን በማስታወቅ፤ ራሳቸውን ማግለላቸውን ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 22 ቀን 2013 ዓ.ም. በትዊተር ገጻቸው አሳወቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ምርጫው በግንቦት መጨረሻ ወይም በሰኔ መጀመሪያ ላይ ይካሔዳል

National Election Board of Ethiopia (NEBE)

ትክክለኛውን ቀን ወደፊት ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል

ኢዛ (ዓርብ ጥቅምት ፳ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 30, 2020)፦ ባለፈው ዓመት 2012፣ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተሸጋገረው ስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ በያዝነው ዓመት 2013 ዓ.ም. ከግንቦት አጋማሽ እስከ ሰኔ አጋማሽ ድረስ ባሉት ሳምንታት ውስጥ ለማካሔድ ውጥን መያዙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አብን የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ሊመራ እንደማይችል አስታወቀ

National Movement of Amhara (NAMA)

የሰልፉ መከልከልና መደናቀፍ እያሟገተ ነው

ኢዛ (ማክሰኞ ጥቅምት ፲፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 27, 2020)፦ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ነው ያለውን “የዘር ፍጅት” ለማውገዝ በአዲስ አበባና በአማራ ክልል ሰላማዊ ሰልፎችን ለማካሔድ ያስተላለፈውን ጥሪ በኃላፊነት መምራት የማይችል መኾኑን አሳውቋል። የንቅናቄው ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም. እስከ ምሽቱ 5 ሰዓት ድረስ ውይይት በማድረግ ባወጣው መግለጫ፤ “በመንግሥት አምባገነናዊ ተግባር ሰልፉን አስተባብሮ በተቋማዊ ማዕከላዊነት ለመምራት ባለመቻሉ” ሰልፉ መሰረዙን ገልጿል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የአሜሪካን አምባሳደርን ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠየቁ

Minister of Foreign Affairs of Ethiopia, H.E. Gedu Andargachew (R) and US ambassador in Ethiopia H.E. Michael Raynor (L), February 13, 2020. (Photo: The Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia)

የፕሬዝዳንቱ ንግግር ጦርነት ቀስቃሽ መኾኑን አሳወቁ

ኢዛ (ቅዳሜ ጥቅምት ፲፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 24, 2020)፦ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ግብጽ የህዳሴ ግድብን ታፈነዳለች በሚል የተናገሩትን አወዛጋቢ ንግግር አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አዲስ አበባ የሚገኙትን የአሜሪካ አምባሳደር በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጧቸው ጠየቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ትራምፕ ግብጽ የህዳሴ ግድብን ታፈነዳለች ማለታቸው ቁጣን ቀስቅሷል

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ

ኢትዮጵያውያን በተጠንቀቅ እንዲቆሙ የሚያመላክት መግለጫ መንግሥት አውጥቷል
ኢትዮጵያውያን አቋማቸውን በተለያየ መንገድ እየገለጹ ነው

ኢዛ (ቅዳሜ ጥቅምት ፲፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 24, 2020)፦ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግብጽ የታላቋ የህዳሴ ግድብን ያፈነዱታል በሚል ያስተላለፉት መልእክት ውዝግብ እየፈጠረ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግሥትና ኢትዮጵያውያን ንግግሩን በመቃወም አቋማቸውን በተለያዩ መንገዶች እየገለጹ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፍትሕ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ተመስገን ደሳለኝ ታሰረ

Journalist Temesgen Desalegn

የመጽሔቱ ዋና አዘጋጁም በፖሊስ እጅ ናቸው

ኢዛ (ረቡዕ ጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 14, 2020)፦ የፍትሕ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ረቡዕ ጥቅምት 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ከቢሮዋቸው ተወስደው መታሰራቸው ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዘምዘም ባንክ የመጀመሪያው ከወለድ ነፃ ባንክ ኾነ

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ (በግራ) ለዘምዘም ባንክ ሥራ መጀመር የሚችልበትን ፍቃድ በሰጡበት ወቅት

ብሔራዊ ባንክ ፍቃዱን አስረከበው
ከአንድ ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር በላይ የተፈረመ ካፒታል አሰባስቧል

ኢዛ (ሰኞ ጥቅምት ፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 12, 2020)፦ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ሲንቀሳቀስ የቆየው ዘምዘም ባንክ ሥራ ለማስጀመር የሚያስችለውን ፍቃድ ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ.ም. ከብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ ተረከበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፌዴራል መንግሥት ከትግራይ ክልል ምክር ቤት ጋር ግንኙነት አቋረጠ

House of Federation and TPLF

የፌዴራል መንግሥቱ ከከተማና ከቀበሌ አስተዳደሮችና ሕጋዊ ተቋማት ጋር ብቻ ግንኙነት ያደርጋል

ኢዛ (ማክሰኞ መስከረም ፳፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 6, 2020)፦ የፌዴራል መንግሥት ከትግራይ ክልል ምክር ቤት እና ከፍተኛ የሕግ አስፈጻሚ አካል ግር ምንም ዐይነት ግንኙነት ማድረግ እንደማይችል የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ መስከረም 26 ቀን 2013 ዓ.ም. ወሰነ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ አካባቢ የሲቪልም ኾነ ወታደራዊ በረራዎችን ከለከለች

Grand Ethiopian renaissance dam

በዚያ አካባቢ ለመብረር ልዩ ፈቃድ መሰጠት እንዳለበት ተገልጿል
የመንግሥት እርምጃ የህዳሴውን ግድብ ድኅንነት ለመጠበቅ ነው

ኢዛ (ሰኞ መስከረም ፳፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 5, 2020)፦ የታላቁ ህዳሴ ግድብ በሚገኝበት የአየር ክልል፤ ከተፈቀደላቸው በረራዎች ውጭ ማንኛውም የሲቪልም ኾነ ወታደራዊ በረራዎች ዝግ መደረጉና መከልከሉ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፕሮፌሰር መስፍን ሥርዓተ ቀብር ነገ ይፈጸማል

Prof. Mesfin WoldeMariam

ከቀብር ሥነ ሥርዓቱ በፊት የሻማ ማብራትና የሽኝት ፕሮግራም ይካሔዳል

ኢዛ (ሰኞ መስከረም ፳፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 5, 2020)፦ የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የቀብር ሥነ ሥርዓት ነገ ማክሰኞ መስከረም 26 ቀን 2013 ዓ.ም. በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ይፈጸማል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ