በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ያለባቸው 11 ደረሰ
ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
አዲስ የተገኙት ኢትዮጵያውያን ናቸው
ኢዛ (እሁድ መጋቢት ፲፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 22, 2020)፦ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ግለሰቦች ቁጥር 11 መድረሱ ተገለጸ።
አዲስ የቫይረሱ ተጠቂ መኾናቸው የተገለጹት ሁለት ግለሰቦች ኢትዮጵያውያን መኾናቸውንም ጤና ሚኒስቴር ዛሬ አስታውቋል።
ላለፉት ቀናት 9 የነበረው የተጠቂዎቹ ቁጥር አሁን አሥራ አንድ የደረሰ ሲሆን፣ ሁለቱ ግለሰቦች ከቤልጅየምና ከዱባይ የመጡ ናቸው። የዛሬው መግለጫ የሚከተለው ነው። (ኢዛ)




