ኮረና ቫይረስ በምርጫ 2012 ጣልቃ ገብቷል
ምርጫው መካሔድ አለመካሔድ እየተመረመረ ነው
ምርጫው መደረግ አለበት፤ የለበትም የሚለው ሙቀት እየተለካ ነው
ኢዛ (ዓርብ መጋቢት ፲፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 20, 2020)፦ በመጪው ነኀሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ይካሔዳል ተብሎ ቀን የተቆረተለት ምርጫ፤ አሁን በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት መካሔድ አለመካሔዱ በምርጫ ቦርድ የሚወሰን መኾኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ገለጻ፤ በኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ምክንያት ምርጫውን ማካሔድ ይቻል እንደኾነ ምርጫ ቦርድ እየገመገመ ስለኾነ፤ የሚደርስበትን ድምዳሜ መሠረት በማድረግ የምርጫው መካሔድ አለመካሔድ የሚወሰን መኾኑን ዛሬ መጋቢት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. ገልጸዋል። (ኢዛ)



