ኢዜማ

ኢዜማ ከምርጫ ቦርድ ያገኘው የሕጋዊ የሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት

ሕጋዊ ሰርቲፊኬቱን የሠጠው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነው

ኢዛ (ኀሙስ ጥር ፳፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. January 30, 2020)፦ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ - ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ በመኾን ለመንቀሳቀስ የሚያስችለውንና ይህንኑ የሚያረጋግጥ የምዝገባና የሕጋዊ የሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተቀበለ።

ከፓርቲው በወጣ መረጃ መሠረት፤ ፓርቲው የምስክር ወረቀቱን (ሰርቲፊኬቱን) የወሰደው በዛሬው ዕለት ነው። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ደግሞ ኢዜማን በአገር አቀፍ ፓርቲነት የመዘገበው ጥር 20 ቀን እንደኾነ ለማወቅ ተችሏል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ