ራማ ሉል (መስፍን አረጋ)
መስፍን አረጋ
ይህ ጦማር (article) በራማ ሉል ላይ (celestial sphere) የሚያተኩር ሲሆን፣ በጨረስኩትና አቅም ሲፈቅድልኝ በማሳትመው ”ጠፈርሲን” (Astronomy) በተሰኘው መጽሐፍ ውስጥ ከሚገኙት ምዕራፎች ውስጥ የተወሰኑ ክፍሎችን በማውጣጣት የተጻፈ ነው።
ጦማር ማለት ጥናታዊ ጽሑፍ እንደማለት ሲሆን፣ ቃሉ የተገኘውም ጦማር (መጽሐፍ፣ ደብዳቤ፣ ክታብ) ከሚለው የግዕዝ ቃል ነው። ጦማር ከሚለው ቃል በመነሳት ደግሞ ጦማረኛ (one who writes articles)፣ ጦማራዊ የሚሉትን ቃሎች እናገኛለን። ግሱም ሲረባ ጦመረ፣ ጡምር፣ ጦማሪ፣ ጡመራ፣ ... እያለ ሲሄድ የእንግሊዝኛ አቻ ግን የለውም። በነገራችን ላይ ጦማር የሚለው እየተለመደና በሰፊው ጥቅም ላይ እየዋለ ነው። ሌሎቹም ቃሎች ጊዜያቸውን ጠብቀው የጦማርን ፈለግ እንደሚከተሉ ቅንጣት ጥርጥር የለኝም። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)



